መስከረም 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጠፈር ተመራማሪዎች በጨረቃ ምሰሶዎች አቅራቢያ ሄማታይት የተባለ የማዕድን ዓይነት (በተለምዶ ዝገት በመባል የሚታወቅ) ማግኘታቸው አስገራሚ ሆኖ ቆይቷል፤ ምክንያቱም ጨረቃ ለዝገት መፈጠር የሚያስፈልጉትን ኦክስጅንና ፈሳሽ ውሃ በብዛት ስለሌላት ነው። አሁን ግን ተመራማሪዎች ለዚህ እንቆቅልሽ መፍትሔ አግኝተዋል።
ሳይንቲስቶች እንደሚጠቁሙት፣ ለዝገቱ መፈጠር የሚያስፈልገው ኦክስጅን ከጨረቃ ሳይሆን ከምድር የላይኛው ከባቢ አየር በፕላኔታችን መግነጢሳዊ ጭራ (magnetotail) ተይዞ በየወሩ ወደ ጨረቃ ይደርሳል።
በቤተ-ሙከራ የተደረጉ ሙከራዎች እንዳረጋገጡት፣ ከምድር የሚመጡት የኦክስጅን አየኖች (ions) የጨረቃን ማዕድናት ወደ ዝገት የመቀየር ኃይል አላቸው ነው የተባለው።
ይህ ያልተጠበቀ ግኝት በምድር እና በጨረቃ መካከል ያለውን የተደበቀ ኬሚካላዊ ትስስር ያሳያል።
ይህ ግኝት ለወደፊቱ የጨረቃ ተልእኮዎች ትልቅ ጥያቄዎችን ያስነሳል። ለረጅም ጊዜ በሚቆዩ የጨረቃ ፍለጋዎች ላይ የመሣሪያዎች እና መዋቅሮች ጥንካሬ እና ዘላቂነት ላይ ትኩረት እንዲሰጥ ያደርጋል ተብሏል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ