መስከረም 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአንዲት እናት ድጋፍና በራሳቸው ጽናት፣ የልጅነት የዕድገት መዘግየትን ተቋቁመው ትምህርታቸውን የተከታተሉት ጄሰን አርዴይ፣ በዓለማችን እጅግ ታዋቂ ከሆኑ የትምህርት ተቋማት አንዱ በሆነው የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ “ታናሹ ጥቁር ፕሮፌሰር” ሆነው በመሾም ታሪክ ሠሩ።
ጄሰን አርዴይ በልጅነታቸው በዕድገት መዘግየት (developmental delays) እና ኦቲዝም ታውቀው ነበር። እስከ 11 ዓመታቸው ድረስ መናገር አልቻሉም ነበር። ማንበብና መጻፍ የተማሩት ደግሞ እስከ 18 ዓመታቸው ድረስ አልነበረም። በችግር ውስጥም ቢሆን ለትምህርት ያላቸውን ፍላጎት ባለመተው፣ ከፍተኛ ጥረት እና ጽናት በማሳየት በአካዳሚክ ዓለም ውስጥ መግፋት ችለዋል ነው የተባለው።
ፕሮፌሰር አርዴይ በአሁኑ ጊዜ በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ሶሺዮሎጂ ፕሮፌሰርነት ቦታ ላይ የተሾሙ ሲሆን፣ ይህ ስኬት በዓለም ዙሪያ ለብዙዎች የመነሳሳትና የማበረታቻ ምንጭ ሆኗል።
የፕሮፌሰር ጄሰን አርዴይ ታሪክ የግለሰቦችን ገደብ የማለፍ ችሎታ እና በችግር ውስጥ ያለውን የሰውን መንፈስ ጥንካሬ የሚያሳይ ነው።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ