መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)አንድ የ19 ዓመት ጀርመናዊ ወጣት የሆነው ዴቪድ ኮሎምቦ ከአገሩ ጀርመን ሆኖ ከ13 በሚበልጡ አገራት የሚገኙ ከ25 በላይ የሚሆኑ የቴስላ (Tesla) መኪናዎችን መቆጣጠር እንደሚችል በመግለጽ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን አስደንግጧል።
ወጣቱ እንዳለው፣ ጠለፋው የተቻለው የቴስላ ደንበኞች የሚጠቀሙበት የቴስላውን ዋና ሲስተም ያልሆነ፣ ነገር ግን ከመኪናው ጋር የተገናኘ የሶስተኛ ወገን (third-party) መተግበሪያ ላይ ያለን የደህንነት ክፍተት በመጠቀም ነው ተብሏል።
ኮሎምቦ ከላፕቶፑ ማድረግ የሚችላቸው የመኪና ተግባራት በሮችን መክፈትና መዝጋት፤ መስኮቶችን ዝቅ ማድረግ፤ ሙዚቃ ማስጀመር፤ የፊት መብራቶችን ብልጭ ማድረግ፤ በመኪናው ውስጥ ሰው መኖር አለመኖሩን ማየት ናቸው ተብሏል፡፡
ሆኖም፣ ወጣቱ መሪውን፣ ብሬክን ወይም የፍጥነት መቆጣጠሪያውን ከርቀት መቆጣጠር አልቻለም።
ቴስላ የኮሎምቦን ታሪክ ባይክድም፣ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች ግን መኪኖች ከውጭ መተግበሪያዎች ጋር ሲገናኙ የሚፈጠረውን ትልቅ አደጋ እንደሚያሳይ ገልጸዋል። ጠለፋው መኪናን አደጋ ላይ ባይጥልም እንኳ፣ በሺዎች ማይሎች ርቀት ላይ ያለ ሰው በሩን መክፈት ወይም ስፒከሩን ድምጽ ከፍ ማድረግ መቻሉ ብዙ ሰዎችን እንዳስደነገጠ ተዘግቧል።
ኮሎምቦ ዓላማው ጉዳት ማድረስ ሳይሆን፣ ችግሩን ወዲያውኑ ለቴስላ በመዘገብ፣ ይህን አስደንጋጭ ግኝት ለመላው የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ወደ ማስጠንቀቂያነት ቀይሮታል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ