መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በተፈጥሮ ውስጥ ከሚስተዋሉ ብርቅዬና አስደናቂ ክስተቶች አንዱ የሆነው ‘አክሊል መሸማቀቅ’ (Crown Shyness) የተባለው ክስተት የባለሙያዎችን ትኩረት ስቧል። ይህ ክስተት በአብዛኛው ረዣዥም ደኖች ውስጥ የሚታይ ሲሆን፣ በአቅራቢያ የሚገኙ የዛፍ ቅርንጫፎችና ቅጠሎች እርስ በርሳቸው ሳይነካኩ በአየር ላይ ልዩ ክፍተቶችን በመተው የጎን ለጎን ዕድገታቸውን የሚያቆሙበት ተፈጥሯዊ ሂደት ነው።
ክስተቱ ከታች ወደ ላይ ሲታይ፣ የዛፎቹ አናት ላይ ያሉት ክፍተቶች ልክ እንደ ተሳሰሩ የእንቆቅልሽ ቁርጥራጮች ሰማዩን ከፋፍለው የሚያሳዩ ጥበባዊና እጅግ ውብ ምስል ይፈጥራሉ።
ሳይንቲስቶች ይህ የዛፎች ባሕርይ የመጣው በዋናነት ራስን ለመጠበቅ ነው ብለው ያስባሉ። ዋና ዋናዎቹ መላምቶችም መካከል የበሽታ እና ተባይ መከላከል አንዱ ሲሆን ቅርንጫፎች አለመነካካታቸው ተባዮችና የበሽታ ምንጮች ከአንዱ ዛፍ ወደ ሌላው እንዳይዛመቱ በመከላከል ለዛፎቹ ጤንነት ይረዳል ነው የተባለው።
ሌላኛው የብርሃንና አየር ዝውውር ሲሆን በእያንዳንዱ ዛፍ ዙሪያ በቂ የሆነ የፀሐይ ብርሃን እንዲደርሰውና በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር በማድረግ ለእድገታቸው አስፈላጊ የሆኑትን ሀብቶች ያረጋግጣል።
ይህ ‘አክሊል መሸማቀቅ’ የተሰኘው ክስተት የረዣዥም ደኖችን አናት ወደ ሕያው ጥበብ በመቀየር፣ የተፈጥሮን ውበት ከመትረፍያ ስልቶች ጋር እንዴት እንደምታጣጥም በተግባር ያሳያል ተብሏል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ