መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የዓለም የታካሚዎች ደህንነት ቀን በላንድማርክ ጠቅላላ ሆስፒታል እየተከበረ ነው።
“ደህንነቱን የጠበቀ የጤና ክብካቤ ለሁሉም ጨቅላ ህፃናት እና ህፃናት” በሚል መሪ ቃል፣ የታካሚ ደህንነትና እንክብካቤን መሠረት ያደረገ ሥራን ለመሥራት ያለመ እንደሆነ ተጠቁሟል።
የላንድማርክ ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ፕሮፌሰር ከበደ ኦሊ፣ የታካሚ ደህንነት ላይ ከፍተኛ ትኩረት አድርጎ መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
በሀገራችን ካለው ከ50 ሺህ በላይ የጤና ተቋማት ውስጥ ከግማሽ በላዩ የግል ተቋማት እንደሆኑ ጠቁመው፣ የህብረተሰቡን የሕሙማን ደህንነት ለመጠበቅ በትጋት መሥራት እንደሚገባ አመላክተዋል።
ፕሮፌሰር ከበደ አክለውም፣ የሕሙማን ደህንነት ሲባል ከሕክምና ቦታ ህንጻ ጀምሮ የአገልግሎት አሰጣጥን እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መስፈርት ሊኖር እንደሚገባ አብራርተዋል። ጥራት ያለው፣ ደህንነቱ የተረጋገጠና የሕሙማንን ደህንነት ያረጋገጠ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የሁሉንም ድርሻ የሚጠይቅ እንደሆነም ተናግረዋል።
በዝግጅቱ ላይ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ፣ እና ከዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮች ተገኝተዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ