መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ዘንድሮም በዓሉ በሚከበርባቸው ሁሉም አከባቢዎች በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ቅድመ በቂ ቅድመ ዝግጅት እንደተደረገ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ጀሚላ ሲምብሩ ተናግረዋል።
የዘንድሮው የኢሬቻ ክብረ በዓል ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ያስታወቁት ኃላፊዋ፣ ይህም አሁን ላይ ሀገሪቱ የደረሰችበትን ደረጃ ለማሳየት ታስቦ ነው ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ በበኩላቸው የዘንድሮው ክብረ በዓል በሠላምና እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ሁሉ ተደርጓል ብለዋል።
ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ያለፈውን መልካም ጊዜ የሚያመሰግንበት ቀጣዩ ጊዜም መልካም እንዲሆንለት የሚለምንበት ነው ብለዋል።
ኢሬቻ መልካ ወደ መልካ ወይም ወንዝ በመውረድ ምስጋና የሚያቀርብበት እንዲሁም መፃይ ጊዜው መልካም እንዲሆን በብራ ወይም በበጋ ወቅት ወደ ተራራ ጫፍ በመውጣት ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል መሆኑን ተናግረዋል።
ሠላም፣ ወንድማማችነት፣ ይቅር ባይነትና አብሮነት የበዓሉ መልካም እሴቶች እንደሆኑም አስታውቀዋል።
በተጨማሪም ኢሬቻ ከአፋን ኦሮሞ እና የገዳ ስርዓት በመቀጠል የኦሮሞ ህዝብ አንድነት ማሳያ መሆኑን የገለጹት የቢሮ ኃላፊው፣ በዘንድሮ ክብረ በዓል ሠላማዊና እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ለማድረግ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ሁሉ መደረጉን አስታውቀዋል።
በዓሉ እሴቱን ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ እና በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስነት እንዲመዘገብ የተጀመረውን ስራ አጠናክሮ ለማስቀጠል ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነጻ በሆነ መልኩ የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ብቻ ማክበር እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተዋል።
የሆራ ፊንፊኔ መስከረም 24፣ የሆራ አርሰዴ ደግሞ መስከረም 25 ቀን 2018 ዓ.ም ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገልጿል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ