መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በአሽከርካሪዎችና በአሰሪ ባለንብረቶች መካከል ይተገበራል የተባለው የስራ ውል በያዝነው 2018 ዓ.ም እንዲተገበር አደርጋለሁ ሲል የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን አስታውቋል።
እንደሌሎቹ የሙያ ዘርፎች በአሽከርካሪዎችና በባለንብረቶች መካከል መደበኛ የስራ ውል ባለመኖሩ ሁለቱም ወገኖች እየተጎዱ ነው ያሉት የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ ናቸው።
ዘርፉን የሚመራው የመንግስት አካል ይህንን የስራ ውል ግዴታ አድርጎ ቢያመጣውም ሙሉ በሙሉ እየተተገበረ አለመሆኑን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ፌደሬሽኑ ከስራና ክህሎት እና ከትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን በተለይ የህግ ማእቀፉ አስገዳጅ ሆኖ እንዲተገበር ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ አቶ ብርሃኔ ገልጸዋል።
በመሆኑም በያዝነው ዓመት ለአሽከርካሪዎች ስልጠና በመስጠት በሁለቱ አካላት መካከል የሚኖረው የስራ ውል ሙሉ በሙሉ መተግበር እንዲችል ለማድረግ ፌደሬሽኑ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
የአሰሪዎችና የአሽከርካሪዎች የስራ ውል እንደ ማንኛውም የስራ ዘርፍ በህጋዊ ውል ውስጥ ማለፍ የሚገባው ነው ያሉት ፕሬዝደንቱ፤ ለሁለቱም አካላት መብትና ደህንነት ሲባል የሚተገበር መሆኑን አጽዕኖት ሰጥተው ተናግረዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ