መስከረም 14 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ቻይና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በታዳሽ ኃይል ልማት ትልቅ ስኬት አስመዝግባለች። ሀገሪቱ በአንድ አመት ውስጥ ከተቀረው ዓለም በሙሉ በላይ የፀሃይ ኃይል የማመንጨት አቅምን ጭናለች።
ይህ ከፍተኛ ዕድገት ደግሞ በተራራማ እና በበረሃማ አካባቢዎች የተዘረጉ ሰፋፊ የፀሃይ ፓነል እርሻዎችን ያካተተ ሲሆን ይህም የፀሃይ ኃይልን የማመንጨት አቅሟን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል ነው የተባለው።
ይህ ፈጣን የፀሃይ ኃይል መስፋፋት ቻይናን በታዳሽ ኃይል ልማት የዓለም መሪ እንድትሆን አድርጓታል የተባለ ሲሆን ምንም እንኳን ቻይና በዓለም ላይ ከፍተኛ የካርበን ልቀት ካላቸው ሀገራት አንዷ ብትሆንም፣ ይህ በታዳሽ ኃይል ላይ የምታደርገው ኢንቨስትመንት ከቅሪተ አካል ነዳጆች ጥገኝነት ለመቀነስ የምታደርገው ጥረት አካል መሆኑ ተገልጿል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ