መስከረም 09 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ሀገራቸው ሰው ሰራሽ አስታውሎትን ያካተተ የጦር ድሮኖችን ማልማት ወታደራዊ ቅድሚያ መሰጠት ያለበት ጉዳይ እንደሆነ መግለጻቸው ተዘገበ።
ኪም ጆንግ ኡን ይህን የተናገሩት በሀገሪቱ ባልተሰየመ ቦታ በተካሄደ የድሮኖች የሙከራ ትርዒት ወቅት ነው። እንደ የሰሜን ኮሪያ ዜና ወኪል (KCNA) ዘገባ ከሆነ፣ መሪው የድሮኖቹን የጦር አጠቃቀም እና ውጤታማነት በተመለከተ ጥልቅ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል። እሳቸውም በውጤቱ በጣም መደሰታቸውን ገልጸው፣ በዘመናዊ የጦርነት ስልት ውስጥ ሰው አልባ መሳሪያዎች ትልቅ ወታደራዊ ሀብት እየሆኑ እንደመጡ ተናግረዋል።
ይህ የኪም መግለጫ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በግንቦት ወር ባወጡት የዩኤስ ወታደራዊ ኢንተለጀንስ ሪፖርት ላይ “ሰሜን ኮሪያ ባለፉት አሥርተ ዓመታት ከነበራት ሁሉ በጠንካራው ስትራቴጂያዊ ቦታ ላይ ትገኛለች” መባሉን ተከትሎ የመጣ ነው። ሪፖርቱ ሀገሪቱ የአሜሪካን ኃይሎችን እና አጋሮቿን አደጋ ላይ ለመጣል የሚያስችላት ወታደራዊ አቅም እንዳላት ገልጿል።
ሰሜን ኮሪያ የድሮን ቴክኖሎጂን ከሩሲያ ጋር ባላት ወታደራዊ ትብብር እያሻሻለች እንደሆነ የሚናገሩ ተንታኞችም አሉ። ለዩክሬን ጦርነት ወደ ሩሲያ የተላኩ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮችም በጦር ሜዳ የድሮን አጠቃቀምን በተመለከተ ልምድ እየቀሰሙ እንደሆነ ይገመታል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ