መስከረም 09 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና ጋር የንግድ ስምምነት ለማድረግ እና የመሪዎች ስብሰባ ለማዘጋጀት እየሞከሩ በመሆናቸው ለታይዋን የሚሰጠውን የ400 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ እንዳገዱት ሪፖርቶች አመልክተዋል። የዋይት ሀውስ ባለስልጣን እንደተናገሩት በወታደራዊ ዕርዳታው ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ገና አልተወሰነም።
ዋሺንግተን ፖስት እንደዘገበው ከሆነ፣ ይህ እርምጃ አሜሪካ ታይዋንን በተመለከተ ለረጅም ጊዜ ስትከተለው ከነበረው ፖሊሲ ያፈነገጠ ነው። በታይዋን ላይ የማያቋርጥ የቻይና ወረራ ስጋት ያለ በመሆኑ፣ አሜሪካ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ለደሴቲቱ የጦር መሳሪያዎች ዋነኛ አቅራቢ ነች።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ለታይዋን ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ወታደራዊ ዕርዳታ አጽድቆ ነበር። ነገር ግን፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአቋማቸው መሰረት፣ አሜሪካ ያለ ክፍያ የጦር መሳሪያ መላክን እንደማይደግፉ የዋሽንግተን ፖስት ዘገባ አመልክቷል። ትራምፕ ከዚህ ቀደም ታይዋን ከአሜሪካ የሰሚኮንዳክተር ኢንዱስትሪን በመውሰድ አሜሪካን እንደጎዳች በመግለጽ የጦር መሳሪያ ዋስትና ለማግኘት መክፈል እንዳለባት ተናግረው ነበር።
የተዘገበው የእርዳታ ማቆም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከቻይና ጋር ያለውን ውጥረት ለማርገብ እየሞከሩ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው ተብሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የቻይና መንግስት ታይዋንን የራሱ ግዛት አድርጎ የሚቆጥር ሲሆን፣ አሜሪካ የጦር መሳሪያ የምታቀርብ ከሆነ “በእሳት እየተጫወተች” ነው በማለት በተደጋጋሚ አስጠንቅቋል።
የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን አስተያየት አልሰጠም። የዩኤስ እና የታይዋን የመከላከያ ባለስልጣናት በቅርቡ በአላስካ ተገናኝተው ድሮኖችን፣ ሚሳኤሎችን እና ሌሎች የባሕር ዳርቻ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን ጨምሮ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚገመት የጦር መሳሪያ ሽያጭ ተወያይተዋል ተብሎ ይታሰባል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
#menahriafm #menahriaradio #መናኸሪያሬዲዮ #መናኸሪያኤፍኤም #ራዲዮ #ሬዲዮ #Radio #fm #menaheriafm #menaheriyafm #addisababa #ethiopia
ምላሽ ይስጡ