መስከረም 09 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በኔፓል ዳንግ ግዛት በሚገኝ ሳታሌ መንደር ውስጥ የሚኖሩት አቶ ቻንድራቢር ኦሊ፣ ለአይነ ስውር ባለቤታቸውና ለስድስት ልጆቻቸው ሲሉ ብቻቸውን 4 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ በመገንባት አስደናቂ ታሪክ ፈጽመዋል።
በቤተሰባቸው መኖሪያ አካባቢ መንገድ ባለመኖሩ ምክንያት፣ ልጆቹ ትምህርት ቤት ለመሄድም ሆነ የጤና አገልግሎት ለማግኘት ይቸገሩ ነበር። ይህንን የቤተሰባቸውን ስቃይ የተመለከቱት አቶ ቻንድራቢር፣ ምንም ዓይነት ማሽንና የገንዘብ ድጋፍ ሳይጠብቁ፣ በመዶሻ፣ በሾፌልና በስለት ብቻ ተራራውን መቅደድ ጀመሩ ነው የተባለው።
ለሰባት ተከታታይ ዓመታት በርትተው በመሥራት፣ የአባታቸውን ፍቅር መታሰቢያ የሆነ መንገድ ገንብተዋል። እያንዳንዱ በመጥረቢያቸው ያረፈ ምት ለልጆቻቸው የወደፊት ሕይወት የተላከ ጸሎት ነበር እየተባለ ነው።
ይህ በገዛ እጃቸው የተሰራው መንገድ የቤተሰባቸውን ሕይወት ከመቀየሩም በላይ፣ ለመንደሩ ነዋሪዎች ሁሉ የሕይወት መስመር ሆኗል። ከዚህ ቀደም ለሰዓታት መጓዝ የነበረባቸው ሰዎች፣ አሁን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ትምህርት ቤትና ወደ ሆስፒታል መድረስ ችለዋል።
የአቶ ቻንድራቢር ኦሊ ታሪክ እውነተኛ ጀግንነትንና በፍቅር የሚመራ ፅናትን ያሳያል። እርሱ እርዳታን አልጠበቀም፣ እርሱ ራሱ እርዳታ ሆነ እየተባለ መነጋገሪያነቱ ቀጥሏል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ