መስከረም 08 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በምዕራብ ፈረንሳይ የሚገኘው ታዋቂው የ”ፑይ ዱ ፉ” የመዝናኛ መናፈሻ፣ ልዩ የሆነ የጽዳት መርሃ ግብር በመጀመሩ የመናፈሻው ጎብኝዎች እየተገረሙ ነው። ስድስት የሰለጠኑ ቁራዎች፣ ከመሬት ላይ የሲጋራ ቆሻሻዎችን እና ትናንሽ ፍርስራሾችን በመልቀም የመናፈሻውን ስፍራ በማጽዳት ተሰማርተዋል።
እነዚህ ብልጥ ቁራዎች፣ የሰለጠኑበትን ቆሻሻ በተለየ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ባስገቡ ቁጥር፣ ወዲያውኑ ምግብ እንደ ሽልማት ያገኛሉ። ይህ ፕሮግራም የሰውን ልጅ የቆሻሻ መጣል ልማድ እንዲያቆም ለማስተማር የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡
የመናፈሻው አስተዳዳሪዎች እንደገለጹት፣ የዚህ ፕሮጀክት ዋና ዓላማ ሰዎች የተፈጥሮን ዓለም እንዲያከብሩ ማስተማር ነው ተብሏል። ምንም እንኳ ቁራዎቹ ሙሉውን ጽዳት ባያከናውኑም፣ በመናፈሻው ውስጥ የሚገኙ ጎብኝዎች ስለ ቁራዎቹ ብልህነት እንዲማሩና የቆሻሻ መጣልን ልማድ እንዲያቆሙ በማበረታታት ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ነው ተብሏል።
የሥነ እንስሳት ተመራማሪዎች እንደሚሉት፣ ቁራዎች ከአእምሯቸው ውስብስብነት የተነሳ በዓለም ላይ ካሉ በጣም ብልህ ወፎች መካከል ይመደባሉ። የእነሱ ችሎታዎች ከሌሎች ወፎች የተለዩ የሚያደርጋቸው ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ ችግር ፈቺ ናቸው፤ የሰውን ፊት መለየትና ማስታወስ ይችላሉ፤አንዱ ከሌላው ይማራሉ እንዲሁም የወደፊት ዕቅድ ማውጣት ይችላሉ ነው የተባለው፡፡
ይህ በፈረንሳይ የተጀመረው ተነሳሽነት፣ የእንስሳትን ብልህነት ለአካባቢ ጥበቃ ለመጠቀም ያስቻለ በመሆኑ፣ ለአለማችን አዲስ የሥራ አመራር ሞዴል ሆኗል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ