መስከረም 07 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)”አሜሪካኖች ዲሞክራሲያቸውን ለማዳን 400 ቀናት ቀርቷቸዋል” የሚለው አባባል በፖለቲካ ተንታኞች ዘንድ ሰፊ ትኩረት አግኝቷል። ይህ አነጋገር በእንግሊዙ ጋዜጣ ዘ ጋርዲያን ላይ ታዋቂው የታሪክ ምሁርና የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ቲሞቲ ጋርተን አሽ በጻፉት ጽሑፍ ላይ የወጣ ሲሆን፣ መጪው የአሜሪካ የምርጫ ዘመን ወሳኝ እንደሆነ ለማሳየት የቀረበ ነው።
ይህ የተወሰነ የቀናት ቁጥር የተሰጠው እ.ኤ.አ. ህዳር 3 ቀን 2026 በሚካሄደው የአሜሪካ የምክር ቤት (midterm) ምርጫ ድረስ የቀሩትን ጊዜ ለማመልከት ነው። ጸሐፊው ምርጫው የአሜሪካ ዲሞክራሲ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ለማሳየት ይህን አኃዝ እንደ ምሳሌ ተጠቅመዋል ነው የተባለው።
የፖለቲካ ተንታኞች ይህ ምርጫ በተለይ ለዴሞክራቲክ ፓርቲ ወሳኝ እንደሆነ ይናገራሉ። የምርጫው ውጤት ፓርቲው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትንና ሴኔትን እንደገና ለመቆጣጠር ያስችለው እንደሆነ ይወስናል። የዴሞክራቲክ ፓርቲ የምክር ቤቶችን ቁጥጥር ማድረግ ከቻለ፣ በአሁኑ ፕሬዚዳንት አስተዳደር ላይ ጠንካራ ቁጥጥር በማድረግ ለዴሞክራሲያዊ ተቋማት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ነው የተባለው።
ጽሑፉ “ይህን ያህል ፍርሃት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሲስፋፋ አይቼ አላውቅም” በማለት ይጀምራል። ይህ አባባል በአሜሪካ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ እየተፈጠረ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ መከፋፈል እና ዲሞክራሲያዊ መርሆች ላይ ስጋት መኖሩን የሚያንጸባርቅ መሆኑ ተመላክቷል።
ብዙዎች ይህንን ምርጫ ለሀገሪቱ የወደፊት አቅጣጫ ወሳኝ ምዕራፍ አድርገው ይመለከቱታል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ