መስከረም 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ሁለት የቲክቶክ ተጠቃሚዎች ፕሬዝዳንቱን የሚያወግዝ ዳንስ በመደነስ የቀረጹትን በማህበራዊ ሚዲያ በማሰራጨታቸው በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።
ወጣቶቹ በቪዲዮው ላይ የፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀመድን ምስል የያዘ ወረቀት ይዘው ሲጨፍሩ መታየታቸውን ተከትሎ፣ የህዝብን ስሜት የመጉዳት እና የፕሬዝዳንቱን ክብር የማዋረድ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ነው የተያዙት። ይህ እርምጃ በአገሪቱ ውስጥ በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና በመንግስት ባለስልጣናት ላይ የሚደረጉ ትችቶችን በሚመለከት ውይይቶችን አስነስቷል፡፡
የሶማሊያ መንግስት ዜጎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚለቋቸውን ይዘቶች እንዲቆጣጠሩ እና ከሀገሪቱ ህጎችና ባህሎች ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ አሳስቧል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ