መስከረም 07 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአካባቢ ላይ በጎ ተጽዕኖ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት፣ ከአናናስ ቅጠሎች የሚሰራ አዲስና ፈጠራ የተሞላበት ቁሳቁስ በአለም አቀፍ ደረጃ ትኩረትን እያገኘ ነው። ይህ ለአሮጌው የእንስሳት እና ሰው ሰራሽ ቆዳዎች እንደ አዲስ አማራጭ የሚቀርበው ቁሳቁስ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ እና ከሥነ-ምግባር አኳያ የተሻለ እንደሆነ ተገልጿል።
ይህ ቁሳቁስ ፒኛቴክስ (Pinatex) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፣ የሚዘጋጀውም በአናናስ ተክል ቅጠሎች ውስጥ ከሚገኙ ረጅም ፋይበሮች ነው ተብሏል። ቀደም ባሉት ጊዜያት እነዚህ ቅጠሎች ፍሬው ከተሰበሰበ በኋላ ይጣሉ ወይም ይቃጠሉ ነበር፣ ይህም ለግብርና ብክነት አስተዋጽኦ ያደርጋል። አሁን ግን እነዚህ ቅጠሎች ዘላቂ እና በቀላሉ የሚበሰብስ ቁሳቁስ ለመስራት እየዋሉ ነው።
የአሰራር ሂደቱ ፋይበሮችን ከቅጠሎቹ ማውጣት እና ማቀነባበር ሲሆን፣ ከዚያም ከእጽዋት በሚገኝ ሙጫ ጋር በመቀላቀል በሽመና ያልተሰራ ጥልፍልፍ ይፈጥራል። በመጨረሻም ይህ ቁሳቁስ የባህላዊ ቆዳን መልክ እንዲይዝ ተደርጎ ይጠናቀቃል ነው የተባለው።
ይህ ፈጠራ የተሞላበት ምርት አስቀድሞ በዲዛይነሮች እና በንግድ ድርጅቶች ዘንድ ጥቅም ላይ መዋል ጀምሯል የተባለ ሲሆን የተለያዩ ምርቶችንም ለመስራት እየዋለ ነው። ከእነዚህም መካከል የእጅ ቦርሳዎች፣ ጫማዎች እና የቤት እቃዎች ይገኙበታል።
ፒኛቴክስ የአካባቢ ጉዳይን ለሚያስቡ ሰዎች ዘይቤያቸውን ወይም ጥራትን ሳይቀንሱ የአካባቢ ተጽኖአቸውን ለመቀነስ የሚያስችል ጥሩ አማራጭ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን የግብርና ቆሻሻን መጠቀም ጥሩ አማራጭ ብቻ ሳይሆን፣ ተረፈ ምርትን ጠቃሚ ሃብት በማድረግ ኢኮኖሚን እንደሚደግፍ ተመላክቷል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ