መስከረም 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በሩሲያ ምድር ውስጥ ጥልቀት ባለው ስፍራ የሚገኘው ግዙፉ ካሊያዚን አርቲ-64 (Kalyazin RT-64) የተባለ የሬዲዮ ቴሌስኮፕ፣ ከቀድሞው የሶቭየት ህብረት ዘመን ትልቅ አሻራ ጥሎ ያለፈ የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ ታሪክ አለው ተብሏል።
ይህ 64 ሜትር ርዝመት ያለው ቴሌስኮፕ በዋናነት የተገነባው ወደ ቬነስና ማርስ በረራ ለማድረግ ከነበሩ ሮቦቲክ መንኮራኩሮች ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ነበር። የሶቭየት ህብረት ከወደቀ በኋላም ቢሆን፣ ቴሌስኮፑ ለሳይንሳዊ ምርምር አገልግሎት መስጠቱን መቀጠሉ ተመላክቷል።
እስከ አሁን ድረስም ለሥነ ፈለክ ጥናትና ከምድር ውጪ ያለውን ህዋ ለመቃኘት ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
ይህ ግዙፍ ግንብ፣ የሰው ልጅ ወደ ኮከቦች ለመድረስ የነበረውን ታላቅ ህልም የሚያስታውስ ነው።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ