መስከረም 06 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ከቀናት በፊት የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለመገናኛ ብዙሃኑ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ካነሷቸው አንኳር ሀሳቦች ውስጥ፤ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች በእንግሊዝ ቋንቋ እያስመዘገቡት ያለው ውጤት ተጨማሪ የቤት ስራን የሚፈልግ ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡መናኸሪያ ሬዲዮም ዘርፉ ላይ እየተነሳ ያለው ጥያቄን አስመልክቶ የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት እና የትምህርት ባለሙያ ሀሳብ ጠይቋል፡፡
የደብረብርሃን መምህራን ትምህርት ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲን ረዳት ፕሮፌሰር መባ ፈጠነ እንደሚሉት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ላይ የሚታዩ ችግሮች መኖራቸው እያሳዩ ካሉ ጉዳዮች ውስጥ የመረዳት አቅም ላይ እያሳረፈ ያለው ተጽዕኖ ነው ይላሉ፡፡አክለውም አሁንም በቋንቋው ላይ መስራት ካልተቻለ ውጤት የማምጣት ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነው ብለዋል፡፡በአሁኑ ሰዓት ከማሰልጠኛ ተቋማት የሚወጡ የእንግሊዘኛ መምህራን ለማስተማር ፍቃደኛ እየሆኑ አይደሉም ብለው፤በዚህም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች ውጤት ላይም ተጽዕኖ አሳድሯል ባይ ናቸው፡፡ተቋማቸው ከእንግሊዘኛ ቋንቋ ጋር በተያያዘ በሙሉ አቅሙ ሙያተኞችን እያፈራ እንደማይገኝ ጠቁመው፤በተቻለ መጠን አራቱ መሰረተዊ ክህሎቶችን በሟሟላት ስልጠና እንዲሰጥ ጥረቶች እየተደረገ መሆኑን አሰገንዝበዋል፡፡
የትምህርት ባለሙያው ዶክተር መስፍን ሞላ ደካማ ውጤት በእንግሊዘኛ ትምህርት ማምጣት የተለመደ ሆኗል ብለዋል፡፡የትምህርት ስርዓቱ ላይ የሚያንዣብቡ ተግዳሮቶችን መፍታት የማይቻል ከሆነም በተለያዩ የትምህርት አይነቶች ላይም ተጽዕኖ እንደሚያሳድርም አስታውቀዋል፡፡በዘርፉ በርካታ የሰው ሀይል ባለመኖሩ፤በክረምት የሚሰጡ ማጠናከሪያ ትምህርቶች ላይ ያለው መቀዛቀዝ ለችግሮቹ ዋነኛ ምክንያት ነው ብለው፤በተቻለ መጠን ችግሩን መፍታት እንዲቻል መምህራኑን በበቂ መንገድ ማሰልጠን እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
ቀደም ባሉ ጊዜያት በትምህርት ተቋማት ቋንቋውን ማሳደግ የሚቻልበት እድል ሰፊ ቢሆንም አሁን ላይ እየተሰራበት እንደማይገኝም ነው የተገለጸው፡፡ ከዚህ ጋር በተገናኘ ትምህርት ሚኒስቴር ከትምህርት ተቋማት ጋር ቋንቋን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎች እንዲከናወኑ ጠቁመዋል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ