ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ዋልተር ኦርትማን የተባሉ ብራዚላዊ አዛውንት በአንድ ኩባንያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በመሥራት የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ሆኑ። በ100 ዓመት ዕድሜያቸውም ለዓመታት ሲያገለግሉት ለነበረው ኩባንያ ታማኝነታቸው እውቅና አግኝቷል።
ዋልተር ኦርትማን ይህንን ክብረ ወሰን ያስመዘገቡት RenauxView በተባለ ኩባንያ ውስጥ ከ84 ዓመታት በላይ በመሥራት ነው ተብሏል። ሥራቸውን የጀመሩት ገና በ15 ዓመታቸው በጥር 17፣ 1938 ሲሆን፣ የረጅም ጊዜ ታሪካቸው በዓለም ሪከርድ መዝገብ ላይ በይፋ መስፈሩን ጊነስ ወርልድ ሪኮርድ ይፋ አድርጓል።
ዋልተር ሥራቸውን የጀመሩት እንደ የመርከብ ጭነት ረዳትነት ነው። በጥረታቸውና ለሥራቸው ባላቸው ፍቅር እየተሸለሙ የኩባንያው የሽያጭ ሥራ አስኪያጅ ለመሆን ችለዋል። ዛሬም በ100 ዓመታቸው ለስብሰባዎች ይቀርባሉ፣ ለሰራተኞች ምክር ይሰጣሉ እንዲሁም የሽያጭ ውሎችን ይዘጋሉ ተብሏል።
የረጅም ጊዜ ስኬታቸው ሚስጥር ምንድነው? ተብለው ሲጠየቁ ዋልተር የሚሰጡት መልስ ቀላል ነው። “የምትወዱትን ሥራ ፈልጉና በሕይወታችሁ ውስጥ አንድ ቀን እንኳን እንደሠራችሁ አይሰማችሁም” ይላሉ። በተጨማሪም ንቁ መሆንን፣ የማወቅ ጉጉትን አለመተውና ከአሉታዊ አስተሳሰቦች መራቅን ይመክራሉ።
የዋልተር ታሪክ ለሥራ ታማኝ ከመሆን በላይ፣ ስለ ሕይወት ዓላማ፣ ፍቅር እና የማወቅ ጉጉት ኃይል ትልቅ ትምህርት ይሰጣል ተብሏል።
በጌታሁን አስናቀ
ምላሽ ይስጡ