ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአለማችን ላይ ብቸኛዋ ቋሚ ነዋሪ የሌላት አህጉር አንታርክቲካ መሆኗ ተገለጸ። ይህች በበረዶ የተሸፈነች አህጉር ምንም እንኳን የሰው ልጅ እንቅስቃሴ የሚታይባት ቢሆንም፣ የሰው ሰፈር ወይም ከተማ የሚባል ነገር የላትም።
የተለያዩ ሀገራት የሳይንስና ምርምር ማዕከላት በአንታርክቲካ ላይ የተቋቋሙ ቢሆንም፣ በውስጣቸው የሚኖሩት ሰዎች ለጊዜያዊ ጥናትና ምርምር ብቻ የሚመጡ ሳይንቲስቶችና ተመራማሪዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች የክረምቱን ጊዜ ጨምሮ ለተወሰኑ ወራት ከቆዩ በኋላ ወደ መጡበት ይመለሳሉ ነው የተባለው።
ከፍተኛ ቅዝቃዜው፣ ለሕይወት የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ነገሮች እጦት እና አስቸጋሪው የአየር ንብረት አህጉሪቱን ለቋሚ መኖሪያነት የማይመች አድርጓታል። በመሆኑም፣ ከምድር ወገብ በታች የምትገኘው ይህች አህጉር በዓለማችን ካሉ የየብስ ክልሎች ውስጥ ለቋሚ ሰፈራ ያልታጨች ብቸኛዋ መሬት ሆና ቀጥላለች ነው የተባለው።
በጌታሁን አስናቀ
ምላሽ ይስጡ