ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባለሥልጣናት እንደገለጹት፣ በአፍጋኒስታን ከፓኪስታን ጋር በሚያዋስነው ድንበር አቅራቢያ እሑድ ምሽት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1,100 በላይ ሆኗል።
ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ መጠኑ 6.0 ማግኒቲዩድ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፣ በአካባቢው በሚገኙ መንደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
የፍለጋ እና የማዳን ሥራዎች በመካሄድ ላይ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ የሟቾች እና የጉዳተኞች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተገምቷል።
በጌታሁን አስናቀ
ምላሽ ይስጡ