ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የመገናኛ ብዙሃን ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት መከላከል ላይ ሊሰሩ እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታውቋል።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከፍተኛ የሆነ የሳይበር ጥቃት ሙከራ እያስተናገደች መሆኑን ያስታወቀው አስተዳደሩ በዚህም የመገናኛ ብዙሀን መረጃዎችን ተደራሽ ከማድረግ ጎን ለጎን ተቋማቸው ለሳይበር ጥቃት እንዳይጋለጥ መስራት እንዳለባቸው ተገልጿል።
ቁልፍ የሳይበር መሠረት ልማቶች አገልግሎት እንዳይሰጡ ማድረግና ማስተጓጎል ፤ የሀሰት ዜናዎችን ማሰራጨት፣ በAI የተደገፉ አሳሳች ይዘቶች፣ ሚስጥራዊ መረጃዎችን መመዝበር፣ ለማይገባው አካል አሳልፎ መስጠት ዋና ዋና ስጋቶች መሆናቸውን ኢንሳ አስታውቋል።
የመንግስት ቁልፍ መሠረተ ልማት፤ የሀገር መለከላከያና የደህንነት ተቋሞች፤ የሳይበር መሠረተ ልማት፤ የኃይል ማሰራጫና መቆጣጠሪያ መሠረተ ልማት ፤ የቴሌኮም አገልግሎት መሠረተ ልማት ፤ የትራንስፖርት አገልግሎት፤ የፋይናንስ ተቋማት መሠረተ ልማት እና የሚዲያ ተቋማት መሠረተ ልማት የሀገር ዋና ዋና ሀብቶች በመሆናቸው ከሳይበር ጥቃት ሊጠበቁ እንደሚገባ ተመላክቷል።
ተቋማቱ የረጅምና የአጭር ጊዜ ስልጠናን በማዘጋጀት ሰራተኞችን ማብቃት ላይ መስራት እንዳለባቸው ተጠቁሟል።
በማሕሌት ሙሉጌታ
ምላሽ ይስጡ