👉 ‘በሕይወቴ እንደ አሁን ጤንነት ተሰምቶኝ አያውቅም’ ብለዋል
ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የጤና ሁኔታቸው እያሽቆለቆለ ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እና በመገናኛ ብዙሃን የተሰራጨውን ወሬ በቁጣ በመቃወም ምላሽ ሰጥተዋል። ትራምፕ በራሳቸው የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ “Truth Social” ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ “በሕይወቴ ውስጥ እንደ አሁን ጤንነት ተሰምቶኝ አያውቅም” ብለዋል።
ይህ የትራምፕ ምላሽ የመጣው ጋዜጠኛ ጋሬት ግራፍ ስለጤናቸው ስድስት ወሳኝ ጥያቄዎችን ካነሳ በኋላ እና ትራምፕ ከህዝብ እይታ ለጥቂት ቀናት ከራቁ በኋላ ነው። ጋዜጠኛው በአካል ላይ የታዩ ምልክቶችን እንደ እብጠት ያለ እግር እና የተጎዳ እጅ እና በባህሪ ላይ የታዩ ለውጦችን በማንሳት ጥያቄዎችን አቅርቦ ነበር።
የኋይት ሀውስ በበኩሉ፣ ትራምፕ በእጃቸው ላይ ያሉት መቁሰል በብዙ የእጅ መጨባበጥ እና አስፕሪን በመውሰድ የተከሰተ እንደሆነ ሲገልጽ፣ የቁርጭምጭሚት እብጠታቸው ደግሞ “ ሥር የሰደደ የደም ሥር እጥረት” (chronic venous insufficiency) በሚባል የተለመደ የጤና ሁኔታ ምክንያት እንደሆነ አብራርቷል።
የፕሬዝደንቱ ምክትል ጄ.ዲ. ቫንስም፣ ትራምፕ በጣም ጥሩ ጤና ላይ እንደሚገኙ እና አስደናቂ ጉልበት እንዳላቸው በመግለጽ የጤና ወሬዎችን ለማጣጣል ሞክረዋል።
ትራምፕ ለበርካታ ቀናት በሕዝብ ፊት ባለመታየታቸው ምክንያት በX (የቀድሞው ትዊተር) ላይ “#TrumpIsDead” የሚለው ሃሽታግ መሰራጨት ጀምሮ ነበር። ሆኖም፣ ትራምፕ ቅዳሜ ዕለት ጎልፍ ሲጫወቱ በፎቶ መታየታቸው ወሬው እንዲበርድ አድርጓል።
ጋዜጠኛ ጋሬት ግራፍ ያነሷቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው
1.የታዩት የእጅ መቁሰል፣ የቁርጭምጭሚት እብጠት እና ሌሎች ምልክቶች ምን ያመለክታሉ?
2.የቅርብ ጊዜ የህዝብ ንግግሮች ላይ የታዩት ግልጽ ያልሆኑ ወይም ወጥነት የሌላቸው የንግግር ዘይቤዎች ምንጭ ምንድነው?
- ከእድሜ ጋር ተያይዘው ሊመጡ የሚችሉ የአእምሮ ችግሮች አሉ ወይ?
4.ትራምፕ በአሁኑ ጊዜ የሚወስዷቸው መድሃኒቶች አሉ? ካሉስ ምን ዓይነት የጎንዮሽ ጉዳት አላቸው?
5.በቀድሞው የጤና መረጃ ላይ ያልተገለጹ አዲስ ህመሞች አሉ?
6.ለምንድነው ስለጤናቸው ሙሉና ዝርዝር መረጃ ለህዝብ የማይቀርበው?
የሚሉ ነበሩ ተብሏል፡፡
ምላሽ ይስጡ