ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ በ8120 የአጭር መልዕክት ማስተላለፊያ ኮድ ኢትዮጵያዊያን በህዳሴው ግድብ ላይ ያላቸውን አስተያየት፣ የተሰማቸውን ስሜትና የእንኳን ደስ አላችሁ! አጭር የፅሁፍ መልዕክት የሚያስተላልፉበት መተግበሪያ ፕሮጀክት ይፋ መደረጉን ታላቁ የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስታውቋል።
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት “የትውልድ አሻራ- ዲጂታል የብስራት መልዕክትና ገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት”ን ዛሬ በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ አስተዋውቋል።
በዚህም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የእጅ ስልኩን በመጠቀም በ 8120 ላይ 20 ብር ብቻ ለግድቡ ድጋፍ በማድረግ የህዳሴው ግድብን በተመለከተ ያለውን መልዕክት ማስተላለፍ እንደሚችል ተመላክቷል።
መርሃ-ግብሩ ከዛሬ ነሃሴ 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት መግለጫ ይጠቁማል።
በአጭር መልዕክት ማስተላለፊያ ኮዱ ላይ ያሉትን የተለያዩ አማራጮችን በመጫንም ከ 5 ብር እስከ 100 ብር ለግድቡ ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻልም ተመላክቷል።
ምላሽ ይስጡ