ነሐሴ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከድርጅቶች፣ ከግለሰቦች እና ከመንግስት ተቋማት የተጣለባቸውን የቅጣት ገንዘብ በማስከበር 404 ሚሊዮን ብር ገቢ ማሰባሰቡን ገልጿል።
ባለሥልጣኑ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ የመዲናዋ ነዋሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት የ2017 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን፣ በተለይም በኮሪደር ልማት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን የደም ማስከበር ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘርሁን አሰፋ ጠቁመዋል።
ይህም በከተማ አስተዳደሩ በተካሄደው የአፈጻጸም ምዘና ላይ ባስመዘገበው የላቀ ውጤት የተነሳ የመኪና ሽልማት እንደተበረከተለት የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ ፣ ይህ ሥራ በያዝነው በጀት ዓመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
በዋናነት ከኅብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ ጥያቄዎች እና የአፈጻጸም ተግዳሮቶች የመልካም አስተዳደር እና የሥነ-ምግባር ችግሮች መሆናቸውን የገለጹት ሥራ አስክያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ይህንን በማሻሻል እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል።
ምላሽ ይስጡ