ነሐሴ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዘመናችን ለተለያዩ መሳሪያዎች መተሳሰሪያነት በስፋት የምንጠቀምበት የብሉቱዝ ቴክኖሎጂ ለሳይበር ወንጀለኞች አዲስ የጥቃት መስመር ሆኖ እየተገኘ መሆኑን የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች አስጠነቀቁ።
አዳዲስ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፣ የብሉቱዝ ግንኙነቶች በተለያዩ ተጋላጭነቶች ምክንያት ለግል መረጃ ስርቆትና ለስርዓት መቆጣጠርያ ሊያገለግሉ ይችላሉ ተብሏል።
ይህ አዲስ የጥቃት ስልት ‘ብሉጃክኪንግ’ እና ‘ብሉስኖፕ’ በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ ሃከሮች በአቅራቢያቸው ከሚገኙ የብሉቱዝ መሳሪያዎች ጋር ሳያውቁት ግንኙነት በመፍጠር መረጃዎችን ለመጥለፍና የጠለፉትን መሳሪያ ለመቆጣጠር ሙከራ ያደርጋሉ ተብሏል።
ባለሙያዎቹ በተለይ በአደባባይ ወይም ብዙ ሰው በሚሰበሰብበት ቦታ የብሉቱዝ ግንኙነቶችን ሲጠቀሙ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በማይጠቀሙበት ጊዜ የብሉቱዝ ግንኙነትን ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት፤የግል እና ሚስጥራዊ መረጃዎችን በብሉቱዝ ከማስተላለፍ መቆጠብ፤ የኮምፒውተርን፣ የስልክን እና የሌሎች መሳሪያዎችን ሶፍትዌሮች ሁልጊዜ በማዘመን (update) ተጋላጭነቶችን መቀነስ እንደሚገባ ተመላክቷል።
የብሉቱዝ መሳሪያዎን የማይታይ (invisible) ማድረግ ወይም ‘discoverable mode’ የሚለውን ማጥፋት ያስፈልጋል ነው የተባለው።
ይህ አዲስ የደህንነት ስጋት ሰዎች የቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸውን እንዲገመግሙና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሚያሳስብ ነው።
ምላሽ ይስጡ