ነሐሴ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጊፍት ሪል እስቴት በለገሀር ሳይቱ 2 ሺሕ ቤቶችን ለሽያጭ ማቅረቡን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።
ከ2ሺህ ቤቶቹ ውስጥ 1ሺህ አምስት መቶዎቹ በሽያጭ ላይ መሆናቸውን የሚናገሩት የሪል እስቴቱ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰለሞን ደበበ 52 ቤቶች ተሸጠው መጠናቀቃቸውንና በ5 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር 550 ሱቆችንና ቤቶች መሸጣቸውንም ተናግረዋል፡፡
ለሽያጩ ከ15 እስከ 25 በመቶ ቅናሽ መደረጉ ያነሱት ሥራ አስፈፃሚው፤ ከነሐሴ 23 እስከ ጳጉሜን 1 ድረስ ሽያጩ እንደሚቆይና ለገዢዎች 45 በመቶ የሚሆን የባንክ ብድር መመቻቸቱን ገልፀዋል፡፡
ሪል እስቴቱ በከተማዋ ለሚኖሩ ምንም አይነት ገቢ ለሌላቸው 30 አባወራዎችና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን ከፍተኛ በጀት በመመደብ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ማድረግ መቻሉን አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡
በመጪው ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ለሚመረቀው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ጊፍት ሪልስቴት ባለሁለት መኝታ የመኖሪያ ቤት ስጦታ በይፋ አበርክቷል።
ከ600 በላይ ሰራተኞችን የሚያስተዳድረው ጊፍት ሪል ስቴት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን በ12 ሳይቶች የመኖሪያ ቤቶችን እየገነባ ሲሆን፤ ከሳይቶቹ መከካል የለገሀር ሳይት አንዱ ነው።
ጊፍት ሪል እስቴት አምስት እህት ኩባንያዎች እንዳሉት የገለፁት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ ሪል ስቴቱ ከተመሠረተ ከ20 ዓመታት በላይ እንደሆነው ተናግረዋል።
ምላሽ ይስጡ