👉የፌደራል ቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከቻይና አጋር አካላት ጋር በጋራ በመሆን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የቴክኒካል ጥገና ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ገለጸ
ነሐሴ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር በአዲስ መልክ የስልጠና ዘርፍ በማመቻቸት የአዳዲስ ቴክኖሎጂን በሚመለከት የተዘጋጁ የስልጠና አይነቶች መኖራቸውን ጠቅሰው ፤ ከነዛ ውስጥ የኤሌትሪክ ተሽከርካሪን ጥገና በተመለከተ በመሰልጠን ላይ ያሉ በርካታ ሰልጣኞች መኖራቸውን ገልጸዋል።
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እየተስፋፉ መሆኑን ተከትሎ ስልጠናው አሁን ላይ በአጫጭር ስልጠና መልክ እየተሰጠ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ፤ በተለይም በቻይና ከሚገኙ አጋር አካላት ጋር በተገባ የጋራ ስምምነት ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ጋር በተያያዘ የቴክኒካል ጥገና ስልጠናው በሃገር ውስጥና በቻይና እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።
የአዳዲስ ቴክኖሎጂን በሚመለከት በተዘጋጁት የስልጠና አይነቶች የሚኖራቸውን ተፈላጊነት ለማጥናት አጫጭር ስልጠናውን በመስጠት እየታየ እንደነበርና ተፈላጊነቱ ከፍ ያለ መሆኑ መረጋገጡን ገልጸው ፤ በጥናቱ መሰረት በቀጣይ በዲግሪ ደረጃ በመደበኛ የስልጠና ዘርፍ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ከኢንስቲትዩቱ በተጨማሪም በግል ተቋማት በኩል እየተከፈቱ ያሉ ማሰልጠኛዎች መኖራቸውን አንስተው ፤ ከግል ተቋማቱም ጋር በትብብር በመስራት ላይ ነን ብለዋል።
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ጥገና አስመልክቶ ሰልጣኝ ወጣቶችን በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገራት ስልጠናዎችን በስፋት እንዲያገኙ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራበት መሆኑን አመላክተዋል ።
ምላሽ ይስጡ