ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቴሌ ሲስተምን በመጠቀም ከግለሰብ አካውንት ብር የሰረቀች የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሏን የሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
የሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የታክቲክ ምርመራ ዲቪዥን ሃላፊ ኢንስፔክተር ታመነች ባሳ እንደገለፁት ፤ አቢሲኒያ አዱኛ የተባለች ይህች ግለሰብ በኢትዮ ቴሌኮም በአዲስአበባ ቅርንጫፍ በኤጀንት አገልግሎት የምትሰራ ስትሆን የአንድን ተበዳይ ሲም ካርድ ዘግታ በማውጣት በቀን 29/11/17 ዓ.ም ከግለሰቡ አካውንት ልትሰርቅ ችላለች፡፡
የሶዶ ከተማ ነዋሪ የሁኑት ግል ተበዳይ ባደረሰው ጥቆማ መሠረት ወንጀሉን የተከታተለው የሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ግለሰቧን ከአዲስ አበባ ከተማ መያዙንም ኢንስፔክተሯ ጨምረው ተናግረዋል።
ምላሽ ይስጡ