ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በጃፓን የ102 ዓመቱ አዛውንት ኮኪቺ አኩዛዋ የፉጂ ተራራን በመውጣት የአለማችን ትልቁ የዕድሜ ባለፀጋ ተራራ ወጪ በመሆን አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግበዋል። የፉጂ ተራራ ርዝመት 3,776 ሜትር (12,389 ጫማ) ነው ተብሏል።
አኩዛዋ ይህን አስደናቂ ታሪክ የሰሩት ከልብ ሕመም ማገገማቸውን ተከትሎ ሲሆን፣ ይህም የብዙዎችን አድናቆትና መደነቅ አግኝቷል። በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን የሰው ልጅ የጤና ገደቦችን ማለፍ እንደሚችል የሚያሳይ ተምሳሌት ሆኗል እየተባለ ነው።
የፉጂ ተራራን መውጣት ለብዙ ወጣት ተጓዦችም ቢሆን ፈታኝ ቢሆንም፣ አኩዛዋ ግን በቁርጠኝነትና በጠንካራ መንፈስ ተራራውን በመውጣት ይህን ታላቅ ስኬት አስመዝግበዋል ነው የተባለው።
ይህ ስኬት ከዓለም ዙሪያ ለብዙዎች ተስፋ እና መነሳሳትን ይሰጣል ተብሎ ይታሰባል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
በጌታሁን አስናቀ
ምላሽ ይስጡ