👉የወንዶች ቁጥር ከሴቶች ይበልጣል?
ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዛሬው ዕለት ባለው መረጃ መሰረት የዓለም ህዝብ ብዛት ከ8.1 ቢሊዮን በላይ ደርሷል። ከዚህ ውስጥ የወንዶች ቁጥር ከሴቶች ቁጥር በጥቂቱ ይበልጣል።
በአሁኑ ሰዓት ወንዶች ከጠቅላላው የዓለም ህዝብ ቁጥር ውስጥ ወደ 50.4% የሚሆነውን ሲይዙ፣ ሴቶች ደግሞ ወደ 49.6% ይሸፍናሉ።
የWorld Population Review መረጃ እንደሚያሳየው በየቀኑ በዓለም ዙሪያ ወደ 209,795 ሰዎች የሚወለዱ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ደግሞ በቀን ወደ 92,610 ሰዎች ይሞታሉ። ይህም የዓለም ህዝብ ቁጥር ያለማቋረጥ እየጨመረ መሆኑን ያመለክታል።
የኢትዮጵያ የህዝብ ብዛት
በተመሳሳይ ከዚሁ ምንጭ በተገኘው መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ አጠቃላይ የህዝብ ብዛት 129,719,301 ደርሷል።
ከዚህ ውስጥ የወንዶች ቁጥር 64,960,632 ሲሆን፣ የሴቶች ቁጥር ደግሞ 64,758,669 ነው። ይህም በኢትዮጵያ ውስጥ የወንዶች ቁጥር ከሴቶች ቁጥር በትንሹ እንደሚበልጥ ያሳያል።
በጌታሁን አስናቀ
ምላሽ ይስጡ