ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቀጣይ አድማስ (Next Horizon) በሚል ሃሳብ የሦስት ዓመታት ስትራቴጂ እቅዱን ተቋሙ በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።
ይህ እቅድ ሲወጣ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ዳሰሳ መደረጉን ፣ከሀገሪቱ ፖሊሲ፣እቅድ እና ሌሎችም ጉዳዮች ጋር በሚጣጣም መልኩ መዘጋጀቱን የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልፀዋል።
አዲሱ ስትራቴጂ የኢትዮጵያን የዲጂታል ለውጥ እውን ከማድረግ አኳያ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ጠቅሰዋል።
ከዚህ ቀደም ተቋሙ ይዟቸው የነበሩ እቅዶችን በስኬት ማጠናቀቁን በመጥቀስ ለአዲሱ ስትራቴጂም ግብዓት መሆኑንም አንስተዋል።
የስትራቴጂው ግብ ትርፍ ማግኘትን ከማስቀደም ይልቅ ሰው ተኮር የሆነ ስራ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አፅንኦት ሰጥተውበታል።
በትዕግስት ተስፋየ
ምላሽ ይስጡ