ነሐሴ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጀርመኗ የሃምቡርግ ከተማ፣ በተለይም በምሽት ህይወቷ ለምትታወቀው ለስትሪት ፓውሊ ወረዳ፣ አዲስና እጅግ አስገራሚ የሆነ የንፅህና አጠባበቅ ዘመቻ ጀምራለች ተብሏል።
የዘመቻው ዋነኛ ዓላማም በከተማው ውስጥ ሲዘወተር የነበረውን የህዝብ ሽንት ችግር በዘላቂነት መፍታት ነው ተብሏል።
ለዚህም ያልተለመደ መፍትሄ፣ አካባቢው ልዩ የሆነ “ሃይድሮፎቢክ” ተብሎ የሚጠራ ቀለም በግድግዳዎቹ ላይ እንደቀባ ተነግሯል።
ይህ ዘመናዊ ቀለም ማንኛውንም ፈሳሽ ነገር ወደ ራሱ የመመለስ ባህሪ ስላለው፣ በግድግዳው ላይ ሽንት የሸና ማንኛውም ሰው ሽንቱ መልሶ ራሱን ላይ እንደሚፈስ ነው የተነገረው።
የዚህም ያልተጠበቀ እርምጃ ዓላማ፣ ሰዎች በግልጽ በሚታዩ ቦታዎች ላይ ሽንት ከመሸናት መቆጠብ እንዳለባቸው ፈጣን የሆነ ቅጣት እና ውርደትን በመፍጠር ማስተማር ነው ተብሏል።
የሃምቡርግ ከተማ ባለስልጣናት ይህ አዲስ እና አዝናኝ ዘዴ የህዝብ ንፅህናን ለማስጠበቅ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
በጌታሁን አስናቀ
ምላሽ ይስጡ