ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኅብረት ሥራ ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀምና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወይዘሮ ሽታዬ መሐመድ እንደገለፁት የኅብረት ሥራ ማኅበራትን በአደረጃጀት በማጠናከርና በማዘመን ማህበራት ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ማድረግ እንደሚገባ አንስተው የኅብረት ሥራ ማኅበራትን በአደረጃጀት ማጠናከርና ማዘመን ይገባል ብለዋል ።
የተጠናቀቀው የበጀት አመት ስኬታማ የሥራ አፈፃፀም የተመዘገበበት ነበር ያሉት ኮሚሽነሯ የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከርና ክፍተቶችን በመሙላት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት ማከናወን እንደሚገባ ተናግረዋል።
በከተማዋ የምርት አቅርቦት ዕጥረት እንዳይፈጠር ከክልሎችና ሌሎች ተቋማት ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር መሥራት እንደሚገባ ጠቅሰው ፤ የሸማች ኅብረት ሥራ ማህበራት የምርት አቅርቦትና ጥራት ማሻሻል ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ በውይይቱ ተነስቷል።
በመድረኩ በበጀት ዓመቱም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የክፍለ ከተማ የኅብረት ሥራ ማህበራት፣ ዩንየኖችና ጽሕፈት ቤቶች እውቅና ተሰጥቷል።
በአስናቀች መላኩ
ምላሽ ይስጡ