ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፈን ሀሰን በመጪው መስከረም ወር ላይ በሀገረ ጃፓን ቶኪዮ ከተማ ላይ በሚከናወነው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ እንደማትሳተፍ ያሳወቀች ሲሆን አስቀድሞ ነሀሴ ወር ላይ በአውስትራሊያ በሚከናወነው የሲድኒ ማራቶን ላይ እንደምትካፈል አሳውቃለች።
ዘንድሮ 35 ሺሕ ሯጮች ይካፈሉበታል ተብሎ የሚገመተው እና በTCS ስፖንሰር አድራጊነት በሚከናወነው የሲድኒ ማራቶን ላይ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ ሲፈን ሀሰን የፊት ገጽ እንደምትሆን ይጠበቃል።
አውስትራሊያ የሯጭ ሀገር ናት ፤ ዜጎቿ በተለያዩ ሩጫ ውድድሮች ላይ እንደሚካፈሉ አውቃለሁ እንደ ሲድኒ አይነት ትልቅ ማራቶን ውድድር ላይ እንደምሳተፍ ስናገር ከታላቅ ደስታ ጋር ነው ስትል ሲፈን ሀሰን ተናግራለች።
ሲፈን ሀሰን አምና በተከናወነው የፓሪስ ኦሎምፒክ በ5ሺህ እና በ10ሺህ ሜትር ርቀት የብር ሜዳሊያ እንዲሁም በማራቶን ርቀት የወርቅ ሜዳሊያ ማስመዝገቧ የሚታወስ ነው።
የጃፓኑ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሲድኒ ማራቶን ከተከናወነ ከሁለት ሳምንት በኋላ ነው የሚከናወነው ከዛ አንፃር ለዝግጅት እና እረፍት ለመውሰድ በቂ ጊዜ ስለማይኖራት የማትሳተፍ ይሆናል።
እ.ኤ.አ ከ2013 በኋላ ሲፈን ሀሰን በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ እንደማትሳተፍ ስታረጋግጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደርገዋል።
በሚካኤል ደጀኔ
ምላሽ ይስጡ