👉ከ10ኛ ፎቅ ላይ ሆኖ መሬት ላይ ያለውን ጉንዳን መመልከት ይቻላል ተብሏል
ነሐሴ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ንስር በአለም ላይ ካሉት ፍጥረታት ሁሉ እጅግ በጣም ከሚሳለዉ እና ከሚገርመው የአይን ብቃት ባለቤት መሆኑን አዲስ ጥናት አመለከተ።
የአይን እይታቸው በሰው ልጆች እይታ ጥራት ከ4 እስከ 8 ጊዜ እንደሚበልጥ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም ለአደን እና ለህልውናቸው ወሳኝ ሚና ይጫወታል ተብሏል።
ይህንን አስገራሚ ችሎታ በምሳሌ ለማስረዳት፣ አንድ ንስር ከ10 ፎቅ ህንጻ ጣሪያ ላይ ሆኖ መሬት ላይ የሚሳበውን አነስተኛ ጉንዳን መለየትና መመልከት እንደሚችል ተመራማሪዎች ገልጸዋል።
የሰው ልጅ ይህ አይነቱን እይታ ቢኖረው ኖሮ የሚለውን ለማሳየትም፣ ንስር ያለውን የዓይን ብቃት ከዚህ ምሳሌ ጋር አነጻጽረውታል።
የንስር ዓይን ይህን የመሰለ ከፍተኛ ብቃት እንዲኖረው ያደረጉት ቁልፍ የሰውነት ባህሪያት መሆናቸውን የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ።
የንስር አይኖች ከራሳቸው ግማሽ ያህል ቦታ የሚይዝ ትልቅ መጠን አላቸው የተባለ ሲሆን ይህ አይን ብዙ ብርሃን የመሰብሰብ እና ዝርዝር ነገሮችን በግልጽ የማየት አቅም ይሰጠዋል ተብሏል።
‘ኮንስ’ የሚባሉት የብርሃን መቀበያ ሕዋሳት በቀለም እይታ እና በጥቃቅን ዝርዝሮች እይታ ውስጥ ትልቅ ድርሻ አላቸው።
የንስር ሬቲና (retina) ውስጥ ያለው የ’ኮንስ’ ሕዋሳት ብዛት ከሰው ልጅ በጣም የላቀ ሲሆን፣ በአንድ ካሬ ሚሊሜትር ውስጥ እስከ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ ኮንስ (cones) አላቸው ተብሏል።
ንስሮች በአይናቸው ውስጥ ሁለት የትኩረት ማዕከሎች (fovea) አላቸው። አንዱ ሰፋ ያለውን ቦታ እንዲመለከቱ ሲረዳቸው፣ ሌላኛው ደግሞ በአንድ ነገር ላይ ብቻ ከፍተኛ ትኩረት በማድረግ ግልጽ አድርጎ እንዲያዩ ያስችላቸዋል ተብሏል።
ይህ አይነቱ የላቀ እይታ ንስር በሰማይ ከፍታ ላይ እየበረረ አዳኙን እንደ ዓሳ፣ ጥንቸል ወይም ነፍሳትን በቅፅበት እንዲያገኝ ያስችለዋል ተብሏል።
በእርግጥም፣ የንስር ዓይን በተፈጥሮ የተፈጠረ ‘እጅግ በጣም የላቀ የርቀት መመልከቻ በመሆን በምድረ በዳው የላቀ የህልውና ጥቅም ሰጥቶታል ነው የተባለው።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
በጌታሁን አስናቀ
ምላሽ ይስጡ