👉መነጸሩ አረንጓዴ ሜዳዎችን እንዲያዩና ብዙ ወተት እንዲያመርቱ ያግዛቸዋል ነው የተባለው
ነሐሴ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሜሪካ በሚገኙ አንዳንድ እርሻዎች ላሞች በረት ውስጥ ሆነው አረንጓዴ ሜዳዎችን እንዲያዩ የሚያስችላቸው የVR መነጽር እየተደረገላቸው ነው ተብሏል፡፡
የመነጸሩ ዋናው ዓላማ የላሞችን የጭንቀት መጠን በመቀነስና ምቾታቸውን በማሻሻል የወተት ምርታቸውን መጨመር ነው ተብሏል።
የVR መነጽሮቹ የሜዳማና ፀሐያማ አካባቢዎችን ምስሎች በማሳየት ላሞቹ ይበልጥ ዘና እንዲሉ ይረዳል የተባለ ሲሆን የመጀመሪያዎቹ የሙከራ ውጤቶችም በወተት ምርት ላይ እንዲሁም በባህሪያቸው ላይ ትንሽ ቢሆንም የሚታይ ለውጥ አሳይተዋል ተብሏል።
በጌታሁን አስናቀ
ምላሽ ይስጡ