ነሐሴ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ ጥናት እንደተረጋገጠው ስኳር የያዙም ሆኑ ስኳር አልባ የሆኑ ለስላሳ መጠጦች ለጤና ከፍተኛ አደጋ ያመጣሉ ተብሏል። እነዚህ መጠጦች እንደ ስኳር በሽታ፣ የልብ ህመም እና የስትሮክ የመሳሰሉ ከባድ የጤና ችግሮች ጋር በቀጥታ የተያያዙ እንደሆኑ ተገልጿል።
ስኳር የበዛባቸው ለስላሳ መጠጦች “ባዶ ካሎሪ” በመባል የሚታወቁ ሲሆን፣ ይህም ምንም አይነት የአመጋገብ ዋጋ ሳይሰጡ ለክብደት መጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። ከዚህም በተጨማሪ እንደ ካንሰር አምጪ ሊሆን የሚችል 4-MEI (4-methylimidazole) የተባለ ኬሚካል እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ አገሮች አጠቃቀሙ የታገደው ብሮሚኔትድ የአትክልት ያሉ ጎጂ ንጥረ ነገሮችን ሊይዙ ይችላሉ ተብሏል፡፡
በሌለ በኩል ደግሞ “ስኳር የለሽ” ተብለው የሚሸጡት መጠጦች ደግሞ የሰው ሰራሽ ጣፋጮች በመጠቀም የሚዘጋጁ ሲሆን፣ እነዚህም ለሰውነት ጎጂ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተመራማሪዎች ያስረዳሉ።
የእነዚህ መጠጦች አዘውትሮ መጠቀም የጣዕም ስሜትን በማደብዘዝ ለጣፋጭ ምግቦች ያለን ፍላጎት እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል ተብሏል። ከዚህም ሌላ የአንጀት ጤናን ሊያዛቡ እና የእንቅልፍ ስርዓትን ሊያውኩ እንደሚችሉ የጥናቱ ውጤቶች ይጠቁማሉ።
ባለሙያዎች ለጤናማ ህይወት ሲባል ከእነዚህ መጠጦች መራቅ ወይም አጠቃቀማቸውን መቀነስ አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
በጌታሁን አስናቀ
ምላሽ ይስጡ