👉ለአንድ ዓመት ተኩል በሕይወት በመቆየት ዓለምን ያስደመመው የዶሮው ተዓምራዊ ታሪክ
ነሐሴ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዘመናት ተዓምር ተብሎ የሚጠራው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰፊው የሚታወቀው የዶሮው አስደናቂ ታሪክ ዛሬም ድረስ መነጋገሪያ ሆኗል።
ይህ የዋይንዶት ዝርያ ዶሮ፣ አንገቱ ከተቆረጠ በኋላ ለ18 ወራት ያህል በሕይወት መቆየቱ ብዙዎችን አስደምሟል።
ታሪኩ የተከሰተው መስከረም በኮሎራዶ ግዛት ፍሩይታ ከተማ ነው። ገበሬው ሎይድ ኦልሰን እራት ለማዘጋጀት ከሚጠበቁት ዶሮዎች መካከል አንዱ የሆነውን ይህን ዶሮ በመጥረቢያ አንገቱን ቆርጦት ነበር ተብሏል።
ይሁን እንጂ መጥረቢያው ማይክን ቢቆርጠውም፣ የደም ሥሩን ሳይነካው እንዲሁም ዶሮው እንዲተነፍስ፣ እንዲዋሃድና አብዛኛው የሰውነት እንቅስቃሴውን እንዲቆጣጠር የሚያስችለውን የአንጎል ግንድ ክፍል እና አንድ ጆሮውን ሳይጎዳው እንደቀረ ተዘግቧል።
ይህም ዶሮ አንገቱ ከተቆረጠ በኋላም ሚዛኑን ለመጠበቅና ለመራመድ እንዲችል አድርጎታል ተብሏል።
የዶሮው ባለቤት በዚህ አስገራሚ ሁኔታ ተደናግጦና ተገርሞ ማይክን ላለመጣል መወሰኑ የተዘገበ ሲሆን ይልቁንም፣ ዶሮውን በአይድሮፐር አማካኝነት ፈሳሽ የበቆሎ ዱቄት እና ውሃ በቀጥታ ወደ ጉሮሮው በመስጠት ይመግበው ነበር ተብሏል።
እንዲሁም በጉሮሮው ውስጥ የሚጠራቀመውን ንፍጥ በማውጣት ህይወቱ እንዲቀጥል ይረዳው ነበር ተብሏል።
የዶሮው አስገራሚ ታሪክ በሰፊው መሰራጨት ጀመረ። የዶሮው ባለቤት ሎይድ ኦልሰን ዶሮውን በመያዝ የተለያዩ ትርኢቶች ላይ ማሳየት ጀመሩ። ዶሮው ሀገራዊ ዝናን በማትረፍ በበርካታ መጽሔቶች ላይ በመታተም በሰፊው ታይቷል።
የተዓምር ዶሮ ተብሎ የሚጠራው ዶሮ በጉዞ ላይ እያለ በአሪዞና ግዛት ፊኒክስ ከተማ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ መሞቱ ተነግሯል።
የዶሮው ባለቤት ሎይድ ኦልሰን የዶሮውን ንፍጥ ከጉሮሮው ለማጽዳት የሚያስችለውን መርፌ (ሲሪንጅ) ባለመያዙ ምክንያት፣ ማይክ በንፍጥ ታንቆ ሕይወቱ እንዳለፈ ተዘግቧል።
ምንም እንኳን ማይክ ቢሞትም፣ የሱ አስገራሚ ታሪክ አሁንም ድረስ በሕይወት አለ የተባለ ሲሆን በየዓመቱ የትውልድ ከተማው በሆነችው ፍሩይታ፣ ኮሎራዶ ውስጥ ‘የራስ-የሌለው ዶሮ ቀን’ የሚል ፌስቲቫል በክብሩ ይከበራል ነው የተባለው።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
በጌታሁን አስናቀ
ምላሽ ይስጡ