ነሐሴ 14 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሁኑ ሰዓት እንደ ኢትዮጵያ ባለ አዳጊ ሀገር በከፍተኛ ሁኔታ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ዜጎች እንዳሉ በተደጋጋሚ ይገለጻል፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የኩላሊት ህመመተኞች በጎ አድርጎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሰለሞን አሰፋ እንደሚሉት የኩላሊት ንቅለ ተከላ የሚያደርጉ ህሙማን ወጪያቸውን ለመሸፈን የገንዘብ የሚሰበስቡቡት መንገድ ለህክምና ሂደቱ ከሚያወጡት በላይ እንደሆነ ለእንግለልት እየተዳረጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በየመንንዱና በተለያየ መንገድ አጭበርባሪዎች ገንዘብ የሚሰበስቡ በመሆኑ ይሄን ለመቆጣጠር የሚያስችል እንዲሁም ታማሚዎች የሚያስፈልጋቸዉን ወጪ በትክክለኛ መንገድ አንዲያገኙ የሚያስችል የእርዳታ መሰብሰቢያ አጭር ቁጥር መዘጋጀቱን እና አገልግሎቱም ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በተፈጠረ ትስስር አማካኝነት የሚውል ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በመዲናዋ ብሎም በተለያዩ የሃገሪቷ ክፍሎች በመዘዋወር የሚደርጉ የእርዳታ ማሰባሰብ ሂደቶች ከህሙማኑ የህክምና ወጪ ይልቅ ለተባባሪ አካላት ወጪ መሸፈኛ በመሆን በፍጥነት ህክምናው እንዳይወስዱ እያደረጋቸው መሆኑንም ዶክተር ሰለሞን አስረድተዋል፡፡
ይህን ችግር ለመፍታት ድርጅቱ የራሱ የሆነ በንግድ ባንክ ላይ ሂሳብ በመክፈት ታካሚዎች እንዲረዱ ለማድረግ ከተቋማት ጋር ንግግር እየተደረገ ስለመሆኑ ጠቁመው ፤በግል እንዲሁም በመንግስት የተቋቋሙ ተቋማትም ከሚያገኙት ደሞዝ እየተቆረጠ ለኩላሊት ታካሚዎች እንዲዉል ማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም ህይወታቸው ካለፉ ሰዎች የአካል ክፍል ልገሳ ማድረግ የሚያስችለው አዋጅ መጽደቁን በማስመልከት የኩላሊት ልገሳ ጉዳይ ሊፈታ ስለሚችል የህክምና ወጪውን ለመሸፍን የሚያግዝ ሁሉም ሰው ሊያውቀው እና ሊጠቀምበት የሚችል ነጻ የጹሁፍ መልክት ቁጥር ከኢትዮ-ቴኮም ጋር በመስማማት ተዘጋጅቶ መጠናቀቁን በመግልጽ አሁን ላይ የቀረው ኢትዮ ቴሌኮም በይፋ ማስጀመሩ ብቻ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ነጻ አጭር የጹሁፍ መላኪያ የገንዘብ መሰብሰቢያ ወደ ስራ ሲገባ ለህሙማኑ የእርዳታ የመሰብሰብ ሂደት እንግልት እና ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ የኩላሊት ህመምትኞች በጎ አድራጎት ድርጅት አመላክቷል።
ምላሽ ይስጡ