ነሐሴ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በፍርድ ቤት ባሳዩት ርህራሄና ቀልድ የተሞላበት ባህሪያቸው “የአሜሪካ ደግ ዳኛ” በመባል በዓለም ዙሪያ የሚታወቁት ተወዳጁ ዳኛ ፍራንክ ካፕሪዮ ከጣፊያ ካንሰር ጋር ለረጅም ጊዜ ሲታገሉ ቆይተው በ88 ዓመታቸው ትናንት ነሐሴ 14 ቀን 2017 ዓ፣ም በሰላም አረፉ።
ዳኛ ካፕሪዮ ከ1985 እስከ 2023 ድረስ የፕሮቪደንስ ከተማ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ ልዩ የዳኝነት ስልታቸው በኤሚ እጩ በሆነው “Caught in Providence” በሚለው የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ታይቷል። ስሜታዊ ፍርዶቻቸው እና ለተከሳሾች ያሳዩት ደግነት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከአንድ ቢሊዮን በላይ እይታዎችን በማሰባሰብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ልብ ነክቷል።
ዳኛ ካፕሪዮ በኖቬምበር 2023 የጣፊያ ካንሰር እንደያዛቸው በይፋ ገልፀው ነበር። ህክምናቸውን በግልጽ ሲያሳውቁ የቆዩ ሲሆን፣ በግንቦት 2024 የኬሞቴራፒ እና የጨረር ህክምናቸውን አጠናቀዋል። ምንም እንኳን በጀግንነት ቢታገሉም፣ ከዚህ ዓለም በሞት ከመለየታቸው በፊት የጤና መጓደል ደርሶባቸው ነበር ተብሏል።
የእሳቸው ውርስ የማይናወጥ ርህራሄ እና በሰዎች መልካምነት ላይ የነበራቸው ጥልቅ እምነት ነው ተብሏል። ዳኛ ካፕሪዮ ባለቤታቸውን ጆይስን፣ አምስት ልጆቻቸውን፣ ሰባት የልጅ ልጆቻቸውን እና ሁለት የልጅ የልጅ ልጆቻቸውን አፍረተዋል ነው የተባለው። የሰብዓዊነት ስራቸው “Filomena Fund” በሚል ስም የተቋቋመውና ችግረኞችን የሚረዳው ድርጅት በኩል ከፍርድ ቤት ባሻገርም ይቀጥላል ተብሏል።
የሮድ አይላንድ ገዥ ዳን ማኪ ሟቹን ዳኛ ለማክበር የመንግስት ባንዲራዎች በግማሽ እንዲውለበለቡ ትዕዛዝ የሰጡ ሲሆን፣ “የሮድ አይላንድ ሀብት” በማለት ገልፀዋቸዋል። በ2025 በታተመው “Compassion in the Court” በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ የተገለፀው የካፕሪዮ የህይወት ታሪክ እና ጥበብ በዓለም ዙሪያ የመልካምነት ተግባራትን ማነሳሳቱን ይቀጥላል ተብሏል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ