ይህ በእንዲህ እንዳለ የአርሰናል ደጋፊዎች የፊታችን ቅዳሜ በሜዳቸው ኤምሬትስ ሊድስ ዩናይትድ በሚያስተናግዱበት የፕሪሚየር ሊጉ 2ኛ ሳምንት ጨዋታን የሚዳኘው ይኸው የሊቨርፑል ደጋፊ መሎኑ እየተገለፀ የሚገኘው ጄረድ ጊለት መሆኑ እንዳሳሰባቸው እና ከወዲሁ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።
አውስትራሊያዊው ጄረድ ጉለት በ2021 ነው በይፋ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች መዳኘት የጀመረው። የFox sportu የጨዋታ ገላጭ ወይም ኮሜንታተር የሆነው ብሬንተን ስፒድ ይሄንን ነገር በአንድ ፖድካስት ላይ በመመስከር መናገሩን ተከትሎ ያንን ንግግር ደግሞ ሊቨርፑል በማህበራዊ ገፃቸው ማጋራታቸው ብዙ ሲያስብል መቆየቱ አይዘነጋም።
ያንን ተከትሎ ዳኛ ጃረድ ጊለት የሊቨርፑል ደጋፊ የመሆን እድሉ ሰፊ ከመምሰሉ ጋር በተያያዘ የሊቨርፑል እና የኤቨርተን የሁለቱ የመርሲሳይድ ክለቦች ጨዋታ እንዳይዳኝ ተደርጓል።
ያንን ተከትሎ ባሳለፍነው መስከረም ወር አርሰናል ወደ ቫይታሊቲ ስቴዲየም ተጉዘው 2-0 በተሸነፉበት ጨዋታ ዊሊያም ሳሊባ የመጨረሻ ሰው ሆኖ ኤቫኒልሰን ላይ የሰራውን ጥፋት በቢጫ ካርድ ቢታለፍም VAR ላይ ተሰይሞ የነበረው ጃረድ ጊለት የእለቱን የመሀል አልቢትር ሮብ ጆንስ ቫር እንዲያይ መልዕክት በማስተላለፍ ሳሊባ የተመለከተው ቢጫ ወደ ቀይ ካርድ ተቀይሮ ከሜዳ መሰናበቱ እና አርሰናልሊል ጨዋታውን መሸነፉ የሚቲወስ ነው።
ታዲያ በአዲሱ የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ኦልድትራፎርድ ላይ በፆኑ ተጋድሎ በጠባብ ውጤት ማንቸስተር ዩናይትድን 1-0 ባሸነፉ ማግስት አዲሱን አዳጊው ቡድን ሊድስ ዩናይትድን በሚያስተናግዱበት ጨዋታ የመሀል አልቢትርነት ሀላፊነቱ የጃረድ ጊለት መሰጠቱ ደጋፊዎቹን ከማስከፋት በላይ ማሰሰቆጣቱን እና ጨዋታችንን ለምን የሊቨርፑል ደጋፊ ይዳኛል በሚል ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።
ጃሬድ ጊለት ሁለቱን የመርሲሳይድ ክለቆች ኤቩእና የሊቨርፑልን ጨዋታ ግን በቀረመው 36 ሳምንቶች እንዳይዳኝ መከልከሉ ግን ተገልጿል።
ሌሎች የፕሪሚየር ሊግ ዳኞች ማለትም ፒተር ባንክስ የኤቨርተን እንዲሁም ወጣቱ እና ምስጉኑ ዳኛ ማይክል ኦሊቨር የኒውካስል ዩናይትድ ደጋፊ መሆኑ ይታወቃል። ያንን ተከትሎ የኒውካስል እና አሁን አዲሱ አዳጊው ክለብ ሰንደርላንድ ጨዋታዎች የማይዳኝ ይሆናል።
ምላሽ ይስጡ