ነሐሴ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር የሚገናኙበት ዕድል እምብዛም እንደሌለ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ገልጸዋል።
በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ሌሎች ምዕራባውያን መሪዎች ግፊት ቢደረግም፣ ሞስኮ ለሁለቱ መሪዎች ቀጥተኛ ስብሰባ ለመያዝ ፈቃደኛ አለመሆኗን አሳይታለች እየተባለ ነው።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ እንደተናገሩት፣ ማንኛውም ድርድር ከመሪዎች ስብሰባ በፊት በባለሙያዎች ደረጃ በጥንቃቄ መዘጋጀት አለበት ብለዋል።
ይህ መግለጫ የሩሲያ እና የዩክሬን የልዑካን ቡድኖች ቀጥተኛ ድርድር እንዲቀጥል ቢደግፍም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ በፑቲን እና በዘለንስኪ መካከል የሚደረግ ስብሰባ እንደማይኖር ፍንጭ ሰጥቷል።
ምላሽ ይስጡ