ነሐሴ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህንን ያለው የአዲስ አበባ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከተለያዩ አካላት ጋር እየመከረበት ባለበት መድረክ ላይ ነው።
የቢሮው ሀላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ እንዳሉት መዲናዋ አሁን ላይ ተፈላጊ ከሆኑ ከተሞች ውስጥ በቀዳሚነት ተጠቃሽ እየሆነች እንደሆነ ጠቁመው ለዚህም የኮሪደር ልማቱን አጋዥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በ2017 በጀት አመትም በተለያዩ ዘርፎች ላይ ቢሮው መሳተፉን እና በዚህም መልካም የሚባሉ አፈፃፀሞችንም ማሳየት እንደቻለም ነው የገለፁት።
የሰላምና ፀጥታ፤የተረጋጋ የገበያ ስርዓት እንዲሁም በትራንስፖርት መስጫ ቦታዎች ላይ የሚታዩ ክፍተቶች እየታረሙ መሆናቸዉ ለአፈጻጸሙ መሳካት አይነተኛ ሚነና እንደተጫወተ አስታዉቀዋል፡፡
አክለውም ቢሮው የሰላም እና ፀጥታ ከሚሰሩ 29 ተቋማት ጋር ፈጥሮት በነበረው ትስስር አማካኝነት መልካም የሆኑ ስራዎችን መስራታ መቻሉንም አስታዉሰዋል፡፡ አያይዘው በበጀት አመቱ ሀይማኖታዊ እና የአደባባይ በዓላትን በተፈለገው ልክ ማሳካት እንደተቻለ እና 340 የሚሆኑ ኹነቶችን በሰላማዊና በተሳካ ሁኔታ ማድረግ እንደተቻለም ጠቁመዋል፡፡
እንዲሁም በበርካታ ጊዜያት ከማህበረሰቡ በቅሬታ፤ በመልካም አስተዳደር የሚነሱ ጥያቄዎችን አግባብነት ባለው መልኩ ምላሽ መስጠት የተቻለበት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
እንደ ማሳያም በመዲናዋ ከተራ አስከባሪዎች ጋር እየተነሱ የነበሩ ቅሬታዎች፤ከደረሰኝ አቆራረጥ እና ነጋዴዎች ሲፈጥሩት የነበረዉን አርቴፊሻል የዋጋ መናርና ለማረጋት የተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤትን ማስመዝገብ እንደተቻለም ነው ያስታወቁት።
ምላሽ ይስጡ