ነሐሴ 14 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)አንድ የናይጄሪያ ብሮድካስተር የጊነስ ወርልድ ሪከርድን ለመስበር አስቦ የሬዲዮ የንግግር ሾውነት ከአራት ቀናት በላይ በማስተላለፍ አዲስ ሪከርድ አስመዝግቧል እየተባለ ነው።
ይህ ስርጭት ለረጅም ጊዜ የተላለፈ የሬዲዮ የንግግር ትዕይንት በመሆን ሪከርዱን ሰብሯል ተብሏል።
የዝግጅቱ አዘጋጅ ይህን ያልተቋረጠ ስርጭት ለማካሄድ ያቀደው፣ የህዝብ ግንዛቤን ለመፍጠር እና በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን ወሳኝ ጉዳይ ለማንሳት እንደሆነ ገልጿል።
ይህ ስኬት በናይጄሪያ የብዙሃን መገናኛ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ክስተት ተደርጎ ሲታይ፣ በአለም አቀፍ ደረጃም ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል ነው የተባለው።
ስርጭቱ እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ በሺዎች የሚቆጠሩ አድማጮችን ማግኘት ችሏል ነው የተባለው።
ብሮድካስተሩ በየመሃሉ ሙዚቃዎች ሲተላለፉ አጭር እንቅልፍ እንደሚተኛ እና ምግብ እንደሚመገብም ተመላክቷል።
ከዚህ ቀደም የረጅም ጊዜ የሬዲዮ ስርጭት ሪከርድ የያዘው ሌላ ብሮድካስተር የነበረ ሲሆን፣ የናይጄሪያው ብሮድካስተር ይህንን በመስበር አዲስ ታሪክ ለመጻፍ ችሏል ተብሏል።
ይህ ሪከርድ በጊነስ ወርልድ ሪከርድስ በይፋ ሲረጋገጥ፣ ብሮድካስተሩ እውቅና ያገኛልም ተብሏል።
ምላሽ ይስጡ