ነሐሴ 14 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)ጀርመናዊው የአጥቂ መስመር ተጫዋች ካይ ሀቨርትዝ ከፍተኛ የጉልበት ህመም እንዳጋጠመው እየተገለፀ የሚገኝ ሲሆን አርሰናል ከወዲሁ በአፋጣኝ አስገዳጅ በሆነ መልኩ ወደ ገበያው በመውጣት መስኮቱ ሴይዘጋ በፊት አንድ የአጥቂ ባህሪን የተላበሰ ተጫዋች ለማስፈረም እንዲሞክሩ ያደርጋቸዋል ሲል ዴቪድ ኦርነስቲን ዘግቧል።
የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን በይፋ ባለፈው ሳምንት ጅማሮውን ሲያበስር አርሰናል ባለፈው እሁድ ከሜዳቸው ውጪ ወደ ኦልድትራፎርድ ተጉዘው ማንቸስተር ዩናይትድን በጠባብ ውጤት 1-0 ባሸነፉበት መርሀ-ግብር 60ኛው ደቂቃ ላይ ጊዮኬሬሽን ተክቶ ወደ ሜዳ በመግባት 30 ደቂቃዎች ያክል መጫወቱ አይዘነጋም።
ያጋጠመው የጉልበት ህመም ለምን ያህል ጊዜ ከሜዳ ያርቀዋል የሚለው ጉዳይ ያልተገለፀ ሲሆን የቡድኑ ክፍት በነበረው የኤምሬትስ ስቴዲየም የዛሬ ልምምድ መርሀ-ግብር ላይ መሳተፍ አልቻለችም።
ጀርመናዊው የአጥቂ መስመር ተጫዋች ከ2025 አንስቶ ያጋጠመው ሁለተኛ ጉዳቱ ሆኖ ተመዝግቧል። ባሳለፍነው የካቲት ወር ዱባይ በሞቃታማ አየር ልምምድ ሲሰራ ከነበረው የአርሰናል ስብስቅ በጡንቻ ህመም ምክንያት ለ3 ወር ለሚጠጋ ጊዜ ከሜዳ ርቆ እንደነበር የሚታወስ ነው።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ቤት የማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ የሚሰለፈው ሌላው ተጫዋች ብራዚላዊው አጥቂ ጋብሬል ሄሱስ አምና ካጋጠመው ህመም በማገገም ላይ ስለሚገኝ በቀጥታ ለቡድኑ በዚ ሰአት አገልግሎት መስጠት አይችልም።
ያንን ተከትሎ መድፈኞቹ ወደ ገበያው በመውጣት አስገዳጅ በሆነ መልኩ አንድ የአጥቂ ባህሪን የተላበሰ ተጫዋች በዚ ሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለማስፈረም ጥረት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
አርሰናል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ያለፉትን 3 አመታት 2ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቃቸው የሚታወስ ነው ፤ ፕሪሚየር ሊጉ ሲቀጥል አርሰናል የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታቸውን የፊታችን ቅዳሜ አዲሱ አዳጊ ክለብ ሊድስ ዩናይትድን በሜዳቸው ኤምሬትስ ምሸት 1:30 ሲል በመጋበዝ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል።
ምላሽ ይስጡ