ነሐሴ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዋናነት የተውትን ዝውውር ነው በድጋሜ እየተመለሱበት የሚገኘው ተብሏል።
እንደሚታወቀው አርሰናል ባለፈው ሀምሌ ወር ከተጫዋቹ ጋር በግል ተስማምተው ከጨረሱ በኋላ በድጋሜ ሀሳባቸውን በመቀየር ስብስባቸው ውስጥ አንገብጋቢ በሆነ መልኩ የሚያስፈልገው Out and out left winger ወይም ተፈጦሮአዊ የግራ መስመር የአጥቂ ተጫዋች መሎኑን ተከትሎ ኤዜ ላይ የነበራቸውን ጠንከር ያለ ፍላጎት አቀዝቅዘው እንደውም እጃቸውን ከዝውውሩ ላይ ማንሳታቸው መገለፁን ተከትሎ እንደ ኤዜ አይነት የማጥቃት እንቅስቃሴ ሊያጠናክር የሚችል ተጫዋች በጥብቅ ሲፈልጉ የሚቆዩት የአርሰናል የከተማ ተቀናቃኝ እና ባለአንጣዎቻቸው ቶተንሀሞች ማርሹን በመቀየር ተጫዋቹ ላይ ፈጥነው በመንቀሳቀስ ከ48 ሰአታት በፊት 60 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወቃል።
ታዲያ ተጫዋቹ ወደ ቶተንሀም አቀና የሚለው ይፋዊ መረጃ በሚጠበቅበት በዚ ሰአት ላይ የካይ ሀቨርትዝ ያልተጠበቀ የጉልበት ጉዳት እንዳጋጠመው መገለፁን ተከትሎ በድጋሜ ፊታቸውኝ ወደ ኤብሬቺ ኤዜ በማዞር የቶተንሀምን ዝውውር በመጥለፍ ፤ ወይም ተጫዋቹን ከመዳፋቸው በመንጠቅ የግላቸው ለማድረግ ከጫፍ መድረሳቸው ነው ዘ አትሌቲክ ለተሰኘው ተነባቢ የሚዘግበው ጋዜጠኛ ዴቪድ ኦርነስቲን መረጃ የሚጠቁመው።
የስፐርሱ አለቃ ዳንኤል ሌቪ እና የክሪስታል ፓላስ እግርኳስ ክለብ Co owner እና Chairman ወይም የክለቡ የከፊል ድርሻ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ስቲቭ ፔሪሽ ጋር በአካል ተገናኝተው መወያየታቸው ቢገለፆም ተጫዋቹ የልጅነት ክለቡን የመቀላቀል ፍላጎቱ የፀና በመሆኑ የአርሰናልን ጥያቄ እንደሚያስቀድም ይጠበቃል።
የተጫዋቹ 68.5 ሚሊዮን ፓውንድ የውል ማፍረሻ ባሳለፍነው አርብ ጊዜው መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን አርሰናሎች ቶተንሀም ለማቅረብ ዝግጁ ከነበሩት 60 ሚሊዮን ፓውንድ እኩል ወይም ከፍ ያለ ሂሳብ ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ይገመታል።
ኤዜ በ2020 QPRን ለቆ ፓላስን የተቀላቀለ ሲሆን ወደ አርሰናል የሚያደርገውን ዝውውር የሚያከናውን ከሆነ የ15 በመቶ የትርፍ ተካፋይ ይሆናሉ።
ኤዜ በሴልኸርስት ፓርክ ቆይታው ባደረጋቸው 146 ጨዋታዎች 34 ጎል ሲያስቆጥር 23 ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። በክለቡ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን ሲያሳኩ ቡድኑን አሸናፊ ያደረገችዋን ብቸኛ ጎል ከመረብ ያሳረፈ ተጫዋች ሲሆን በሁለት ሳምንት በፊት መጋረጃ ገላጩን የኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ ሊቨርፑልን በመርታት ከክለቡ ፓላስ ጋር ማሳካቱ የሚታወስ ነው።
ክሪስታል ፓላስ በኮንፈረንስ ሊግ የፔሌይ ኦፍ ጨዋታቸው ላይ ይሰለፋል ተብሎ የሚጠበቀው ሲሆን በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ከኖቲንጋም ፎረስት ጋር በሚደደርገው የሴልኸርስት ፓርኩ የፕሪሚየር ሊግ የ2ኛ ሳምንት ጨዋታ ኤብሬቺ ኤዜ የመጨረሻ ጨዋታውን ለፓላስ ያደርጋል ፤ የክለቡን ደጋፊዎችም ይሰናበታል ተብሎ ይገመታል።
ምላሽ ይስጡ