ነሐሴ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የስፔኑ ተወካይ ቡድን የክለባቸው ሪከርድ በሆነ ዋጋ ወይም 29.5 ሚሊዮን ዩሮ ለቼልሲ ወጪ የሚያደርጉ ይሆናል።
ይህ ተጫዋች ከሰሞኑ የቼልሲ ውዝግብ የተሞላበት የዝውውር ፖሊሲ ገፈት ቀማሹ ነው። ማለትም ሬናቶ ቬይጋ ባሳለፍነው ክረምት ወር መስኮት ላይ ባዜልን በመልቀቅ የምዕራብ ለንደኑን ክለብ መቀላቀሉ አይዘነጋም። ዝውውሩ ግን ተጫዋቹን ዋጋ ያስከፈለ ጉዳይ ሆኗል።
ተጫዋቹ ሁለገብ ተጫዋች ነው። ይህ ፖርቹጋላዊ በቀኝም በግራም ተመላላሽ የተከላካይ ስፍራ ቦታ እንዲሁም የመሀል ተከላካይ ስፍራ ቦታ ላይም ተሰልፎ መጫወት ይችላል።
22 አመቱ ላይ ነው የሚገኘው ይህ ፖርቹጋላዊ የቼልሲ ቆይታው አሁን አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ቤን ቺልዌል ሁነኛ ተተኪ የመሆን አቅም እንዳለውም ታምኖበት ነበር ስታም ፎርድ ብሪጅ የደረሰው። አሁን ግን ክለቡ ለሱ በሚሰጡት የጨዋታ ጊዜ ማነስ እና የመሰለፍ ውስንነት ደስተኛ አለመሆኑ ሲገለፆ ቆይቷል።
ሜትር ከ 93 ስለሚረዝም ለቡድን የቆመ ኳስ የመከላከል ጥራትም ትልቅ ሚና እንደሚወጣ ይገመታል። ለፖርቹጋል 21 አመት በታች ቡድን ተሰልፎ የተጫወተ ሲሆን በአሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ለሚሰለጥነው ዋናው ቡድንም ጥሪ ደርጎለት በአውሮፓ ዋንጫ እና ኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ሀገሩን መወከል ችሏል።
ከስፖርቲንግ ሊዝበን ወደ ባዜል ወደ 4.6 ሚሊዮን ዩሮ ወጥቶበት ካቀና በኋላ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በድምሩ 26 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል። ዘንድሮ ግን በአሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ስር የመሰለፍ እድልን በማጣቱ ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ ራሱ ተጫዋቹ ከአንደበቱ ይህንን ነገር መናገሩ አይዘነጋም።
ጁቬዎች በሴሪያ ጠንካራው የተከላካይ መስመር ባለቤት ቢሆኑም ይበልጥ ስብስቡን የማጠናከር ፍላጎት በማሳየት በዋናነት ከተከላካይ መስመር ተጫዋቾች ጋር ቢያንኮኔሪዎቹ ስማቸው ሲያያዝ ከቆየ በኋላ ተጫዋቹ ጁቬን የመቀላቀል ምርጫው ማድረጉን ጂያንሉካ ዲ ማርዞ እና ፋብራዝዮ ሮማኖ መዘገባቸው አይዘነጋም።
ጁቬ ተጫዋቹን ለ6 ወር ለመዋስ 3.8 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 2 ሚሊዮን ፓውንድ የሚከፍሉ ይሆናል። ባሳለፍነው የውድድር ዘመኑ እስኪጠናቀቅ ድረስ ተጫዋቹ በቋሚነት አሊያንዝ የሚቆይበት አማራጭ አይኖርም ወደ ቼልሲ የሚመለስ ይሆናል ፤ የክለቦች የአለም ዋንጫ ላይ የቼልሲ ስብስብ አካል ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ በማሬስካ አሁንም ጀርባው የተሰጠው ተጫዋች መሆኑን ተከትሎ ከቡድኑ ጋር ወደ አሜሪካ አላቀናም።
ባሳለፍነው ሰኔ ወር ከሀገሩ ፖርቹጋል ጋር በመሆን ስፔንን በመለያ ምት በማሸነፍ የኔሽንስ ሊግም ለሁለተኛ ጊዜ ያሳካው ቡድን ውስጥ እንደነበር የሚታወስ ነው።
የቀጣይ የውድድር ዘመን የስብስቡ አካል የሚሆንበት እድልም ጠባብ ነው ከዛ አንፃር ክለቡን አሁን መልቀቅ እንደሚፈልግ ነው Football espana በፊት ገፃቸው ላይ ይዘውት የወጡት መረጃ የሚያመላክተው።
ቢጫ ሰርጓጆቹ ቪላሪያሎች የተጫዋቹ መዳረሻ ሆነዋል። ክለቡ የስፔን ላሊጋ የውድድር ዘመናቸውን ሪያል ኦቪዶን 2-0 በማሸነፍ ቢጀምሩም በዝውውር መስኮቱ የቡድኑ የማጥቃት እንቅስቃሴ ዋና አድራጊ ፈጣሪው ተጫዋች አሌሀንድሮ ባይና አትሌቲኮ ማድሪድን እንደተቀላቀለ የሚታወስ ነው።
አጥቂአቸው ቲዬርኖ ባሪም ኤቨርተንን መቀላቀሉ የሚታወስ ነው። ቶማስ ፓርቴን በነፃ ከአርሰናል ማግኘታቸው ይቲወቃል አሁን ደግሞ ሬናቶ ቬይጋን የክለባቸው ሪከርድ የሆነ ዋጋ በማውጣት ተጫዋቹን የግላቸው ማድረጋቸው ተረጋግጧል።
ቼልሲዎች አሁንም ትርፋማ ቢዝነስ ስለመስራታቸው መናገር ይቻላል ተጫዋቱን ከአንድ አመት በፊት በ12 ሚሊዮን ፓውንድ ማስፈረማቸው የሚታወስ ሲሆን በ29 ሚሊዮን ዩሮ በመሸጥ ጥሩ ትርፋማ ያደረጋቸውን ቢዝነስ ሰርተውበታል።
ሬናቶ ቬይጋ ለቼልሲ በፕሪሚየር ሊጉ 7 ጨዋታዎች ላይ ብቻ መሰለፍ የቻለ ተጫዋች ነው።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ