ነሐሴ 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቅርቡ በቱርክሚስታን ከተማ አዋዛ የተደረገው ባህር የሌላቸው ታዳጊ ሀገራት ጉባኤ የፀደቀው የአዋዛ ስምምነት በጂኦግራፊ አቀማመጥ ምክንያት ባህር የሌላቸው ታዳጊ ሀገራት ባህር እንዲያገኙ የሚያስችል ሀገራት ቀጠናዊ ውህደት በመፍጠር አብሮ እንዲያድጉ የሚያደረግ ስምምነት እንደሆነ ይታወቃል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያን በመወከል በጉባኤው ላይ የታደሙት ዶክተር ፈቲህ መሃዲ ለመናኸሪያ ሬዲዮ እንደተናገሩት ስምምነቱ የተባበሩት መንግስታት ቻርተርን ተቀብለው ፈርመው አባል በሆኑ ሀገራት የመፍትሄው አካል እንዲሆኑ ይጠበቃል ያሉ ሲሆን በተለይ ኢትዮጵያ እያነሳች ያለችዉን ጥያቄ ጎረቤቶቿ ተቀብለው የመፍትሄ አካል ሊሆኑ ይችላሉ ወይ ብልን ላቀረብንላቸው ጥያቄ የዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን ማሳደር እና የተባበሩት መንግስታት ሰነዱ እንዲተገብር እንዲያደርግ የዉትወታ ስራን መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ የባህር በርን በተመለከተ እያቀረበች ያለችው ጥያቄ ያልተገደበ የባህር አገለግሎት ጥያቄ መሆኑን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባህር የሌላቸው ታዳጊ ሀገራት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ፍላጎቷን በግልጽ ማቅረቧን የጉባኤ ተሳታፊ ዶክተር ፈቲህ መሃዲ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡ በጉባኤው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም በግልጽ የተንፃባረቀበት ውይይት እንደነበርም አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡ በጉባኤው ላይ ከተሳተፉ ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ በልዩነት ወደብ የነበራትና በባለፉት ሰላሳ አመታት ውስጥ ወደብ አልባ መሆኗን በቅርብ ርቀት ላይም ወደብ ባለበት አካባቢ ያለች በመሆኑ ፤ ለደህንነቷና ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር መያዟን በማመላከት የግድ ያልተገደበ የወደብ አገልግሎት ልታገኝ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ማስረዳታቸውን ዶክተር ፈቲህ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልፀዋል፡፡
በጉባኤው ላይ የቀረበው አዋዛ ሰነድም ይህንኑ ጥያቄ የሚያበረታታ ታዳጊ ሀገራት ባህር በር ስለሌላቸው እድገታቸው ላይ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችና መፍትሄ ሃሳቦችን የሚያመላክት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
አሁን ላይ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ዓለም አቀፋዊ አጀንዳ መሆኑና በዓለም አቀፍ መድረክ አጀንዳ እንዲሆን ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ