ነሐሴ 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በልዩ አደን ዘዴው እና በሚያስፈራ ቁመናው የሚታወቀው ሹቢል ስቶርክ (Shoebill Stork) የተባለው ወፍ፣ በአራት ጫማ የሚበልጥ ቁመቱ እና ዓይኑን ሳያረግብ ከ20 ደቂቃ በላይ ሊቆይ በሚችለው እይታው ለሌሎች እንስሳትና አጥማጆች አስፈሪ የሆነ አዳኝ እንደሆነ ተገለጸ።
ይህ ወፍ “የሞት ወፍ” (Death Bird) በሚል ቅጽል ስምም ይታወቃል የተባለ ሲሆን ይህ አስፈሪ ዝምታ የሹቢል ስቶርክ የጥቃት ስልት ቁልፍ አካል ነው እየተባለ ነው።
ወፉ በዙሪያው ካለው ተፈጥሮ ጋር በመመሳሰል፣ እንደ ቅርጻቅርጽ ለረጅም ጊዜ እንቅስቃሴ አልባ ሆኖ ይቆያል። ይህ ድንገተኛ እንቅስቃሴ አልባነት አዳኙን ለማጥቃት የሚያስችለውን ትክክለኛ ጊዜ እንዲጠብቅ ያስችለዋል ነው የተባለው።
አንዴ አዳኙ በአቅራቢያው ሲመጣ፣ ሹቢል ስቶርክ በከፍተኛ ፍጥነትና በትክክለኛነት በመንቀሳቀስ ጥቃቱን ይሰነዝራል ነው የተባለው።
የዚህ ወፍ አስገራሚ የአደን ዘዴ እና ልዩ ባህሪው በተፈጥሮ አለም ውስጥ ካሉ እጅግ በጣም አስደናቂ አዳኞች አንዱ ያደርገዋል ተብሎለታል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ