ነሐሴ 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አውስትራሊያ የእስራኤል ፖለቲከኛ የሆኑት ሲምቻ ሮትማን ወደ ሀገሪቱ ለመግባት ያመለከቱትን ቪዛ መሰረዟን አስታውቃለች።
የአውስትራሊያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ቶኒ ቡርክ ሮትማን ወደ አውስትራሊያ የሚገቡበትን ቪዛ የሰረዙት “መከፋፈል ለመፍጠር” አስበዋል በሚል ክስ ነው።
ሮትማን በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መንግስት ውስጥ የፓርላማ አባል ናቸው። በአውስትራሊያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ቡርክ የተሰጠው መግለጫ እንዳመለከተው፥ “የኛ መንግስት ወደ ሀገራችን መጥተው መከፋፈል ለመፍጠር በሚፈልጉ ሰዎች ላይ ጠንካራ አቋም አለው” ብለዋል። አክለውም “የጥላቻ እና የመከፋፈል መልእክት ይዘው ወደ አውስትራሊያ የሚመጡ ከሆነ አንፈልጋችሁም” ሲሉ አስረድተዋል።
ይህ ውሳኔ የመጣው እስራኤል እና አውስትራሊያ በአጠቃላይ በፍልስጤም እና እስራኤል ጉዳይ ላይ ውጥረት ባለበት ወቅት ሲሆን፣ አውስትራሊያ በሚቀጥለው ወር የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነጻ የፍልስጤም መንግስት እንደምትደግፍ ከገለጸች በኋላ ነው።
የሮትማን ቪዛ መሰረዝ በእስራኤል መንግስት ዘንድ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፣ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዴዎን ሳር የአውስትራሊያን ተወካዮች የፍልስጤም አስተዳደር ውስጥ ለመኖር የተሰጣቸውን ቪዛ እንደሰረዙ መግለጻቸውን ዘገባው ያመለክታል።
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዴዎን ሳር አውስትራሊያ ፍልስጤምን ለመቀበል የወሰነችው ውሳኔ አክለውም የሮትማን ቪዛ መሰረዝ “አስጸያፊ እና ተቀባይነት የሌለው” ሲሉ አውስተዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ